​ሚካኤል ደስታ ወደ መቐለ ከተማ አምርቷል

ሚካኤል ደስታ ከመከላከያ ጋር የነበረውን ቀሪ የአንድ አመት ውል በስምምነት አፍርሶ ወደ መቐለ ከተማ አምርቷል፡፡ ከ10 አመታት በኋላም ወደ መቐለ ተመልሷል፡፡

ሚካኤል በ1990ዎቹ ከመቐለው ክለብ ትራንስ ኢትዮጵያ ጋር የተሳኩ ጊዜያትን አሳልፎ በአዲሱ ሚሌንየም ወደ ኢትዮጵያ መድን ያመራ ሲሆን በ2002 ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ አምርቶ ሁለት የውድድር ዘመናት በፈረሰኞቹ ቤት አሳልፏል፡፡ ከ2004 ጀምሮ በቆየበት መከላከያም የመጨረሻዎቹን 3 አመታት ቡድኑን በአምበልነት መምራት ችሏል፡፡

አዲሱ የሊጉ ክለብ መቐለ ከተማ ሚካኤል ደስታን ጨምሮ 14 ተጫዋቾችን ማስፈረም የቻለ ሲሆን ይህም ከፕሪምየር ሊጉ ክለቦች መካከል በክረምቱ የዝውውር መስኮት በርካታ ተጫዋቾች በማስፈረም ቀዳሚ ያደርገዋል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *