​የሴቶች ፕሪምየር ሊግ መርሀ ግብር እና የውድድር ደንብ ይፋ ሆኗል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የ2010 ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ1ኛ እና 2ኛ ዲቪዚዮን ድልድል እጣ ማውጣት ሥነ ስርሃት ዛሬ በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል አከናውኗል፡፡ ለሶስት አመታት የሚያገለግለው የሊጉ የመተዳደሪያ ደንብም ለክለብ ተወካዮች የቀረበ ሲሆን በደንቡ ላይ አዳዲስ ጉዳዮች ገለፃ ተደርጎባቸዋል፡፡

በሊጉ ላይ የሚወዳደሩ ክለቦች በ2009 ዓም ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት ለሁለት የዲቪዚዮን እርከኖች መከፈላቸው እና ስያሜያቸውም የ1ኛ ዲቪዚዮን እና 2ኛ ዲቪዚዮን መሆኑ ተገልፃል፡፡

ከ1ኛ ዲቪዚዮን የሚወርዱ እና ከ2ኛ ዲቪዚዮን የሚወጡ ክለቦች ብዛት ሁለት እንዲሆኑ ፌደሬሽኑ ለክበቦች ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ክለቦች ግን ሳይስማሙበት ቀርቷል፡፡

በ1ኛው ዲቪዚዮን ላይ ከሚሳተፉ ክለቦች ውስጥ 9ኛ እና 10ኛ የሚወጡ ክለቦች ወደ ታችኛው የዲቪዚዮን እርከን እንደሚወርዱ ሲገለፅ ከ2ኛው ዲቪዚዮኝ ደግሞ አራት ክለቦች እንደሚያድጉ እና በ2011ዓም12 ክለቦች በ1ኛው ዲቪዚዮን ላይ እንደሚሳተፉ ተነግሯል፡፡

ከክለብ ተወካዮች በርካታ ሃሳቦች የተነሱ ሲሆን በተለይ የውድድር መራዘም እና ለጨዋታ ምቹ ሰዓት አለመምረጥ፣የዳኞች ምደባ እና የተጨዋቾች የዝውውር ገንዘብ አከፋፈል መንገድ ላይ ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን በችግሮች ላይ የመፍትሄ ሃሳቦች ቀርበዋል፡፡

ከውይይቱ በኃላ የሁለቱም ዲቪዚዮኖች የእጣ ማውጣት ስነስርዓት የተከናወነ ሲሆን በአንደኛው ዲቪዚዮኝ 10 በሁለተኛው ዲቪዚዮን ደግሞ 12 ነገር ግን ተጨማሪ ክለቦች የሚመጡ ከሆነ እንደሚጨመሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የመጀመሪያ ሳምንት የአንደኛ ዲቪዚዮን መርሃ ግብር

ሲዳማ ቡና ከ መከላከያ

ድሬዳዋ ከተማ ከሃዋሳ ከተማ

ደደቢት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጌድዮ ዲላ

አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የመጀመሪያ ሳምንት የሁለተኛ ዲቪዚዮን መርሃ ግብር 

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ከ አቃቂ ክ/ከተማ

ጥረት ኮርፖሬት ከንፋስ ስልክ ክ/ከተማ

ቄርቆስ ክ/ከተማ ከአ.አ ከተማ

ጥሩነሽ ዲባባ ወጣቶች ማሰልጠኛ አካዳሚ ከቦሌ ክ/ከተማ

ልደታ ክ/ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና

አርባምንጭ ከተማ ከቅ/ማርያም ዩንቨርስቲ

ፌደሬሽኑ ውድድሩ ጥቅምት 11 እንደሚጀምር ማስታወቁ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ስብሰባ ላይ ግን የሁለቱም ዲቪዚዮኖች የመጀመሪያ ቀን ወደ ጥቅምት 27 እንደተገፋ ለማወቅ ተችሏል፡፡የሜዳዎች አለመመቸት አሁንም ከጥቅምት 27 ወደ ህዳር 4 ሊገፋው እንደሚችል ሲጠቆም ይህ ግን የሚሆነው አስገዳጅ ሁኔታ ከመጣ ቡቻ መሆኑ ተነግሯል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *