​ወላይታ ድቻ የቻድ ዜግነት ያለው ተከላካይ አስፈርሟል

ወላይታ ድቻ በቅድመ ውድድር ዝግጅት ወቅት ከቡድኑ ጋር የሙከራ ጊዜ እያሳለፈ የነበረው ቻዳዊው የመሀል ተከላካይ ማሳማ አሴልሞን በ1 አመት ውል አስፈርሟል፡፡

የ28 አመቱ የመሀል ተከላካይ በትውልድ ሀገሩ ክለብ ፎውላ ኢድፊስ ከ2007 እስከ 2013 የተጫወተ ወደ ጋቦን በማቅናትም ለዩኤን ስፖርቲቭ ዲ ቢታ እና ሲኤፍ ሞናና ክለቦች ተጫውቷል፡፡ ተጫዋቹ ለቻድ ብሔራዊ ቡድን ከ15 በላይ ጨዋታዎች ማድረግ ሲችል በአንዳንድ ጨዋታዎችም ቡድኑን በአምበልነት መርቷል፡፡

በዝውውር መስኮቱ ከሌላው ጊዜ በተለየ በርካታ ተጫዋቾች እያስፈረመ የሚገኘው ወላይታ ድቻ እስካሁን አሴልሞን ጨምሮ ሶስት የውጪ ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾችን በቡድኑ አካቷል፡፡ በቀጣዮቹ ጊዜያትም ተጨማሪ የመስመር አጥቂ እና አማካይ ሰፍራ ተጫዋቾች ከውጭ ለማምጣት ጥረት ላይ እንደሆኑ የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ሀሲሶ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *