ካስቴል ዋንጫ ፍጻሜ፡ ሲዳማ ቡና ከ አርባምንጭ ከተማ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FT ሲዳማ ቡና  0-1  አርባምንጭ ከተማ 

39′ ላኪ ሳኒ


ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በአርባምንጭ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ አርባምንጭ ከተማ – የ2010 የደቡብ ካስቴል ዋንጫ ቻምፒዮን!

የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ
90+7′ ወንድሜነህ ዘሪሁን ወጥቶ ብሩክ ዋኮ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ
89′
ግሩም አሰፋ ወጥቶ አብይ በየነ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ
88′
የአርባምንጩ ግብ ጠባቂ በደረሰበት ጉዳት በሲሳይ ባንጫ ተቀይሮ ወጥቷል

77′ ወንድሜነህ አይናለም ከፍጹም ቅጣት ምት ክልል ጠርዝ የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ
75′
ዮናታን ከበደ ወጥቶ አስጨናቂ ጸጋዬ ገብቷል

የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ
72′
ክፍሌ ኪአ ወጥቶ ትርታዬ ደመቀ ገብቷል

የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ
70′
አምሀ በለጠ ወጥቶ ወንድሜነህ አይናለም ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ
68′
ላኪ ሳኒ ወጥቶ ገብረሚካኤል ያዕቆብ ገብቷል

ቢጫ ካርድ
64′
ምንተስኖት አበራ በሰራው አደገኛ ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

62′ አብዱለጢፍ መሀመድ በጥሩ የማጥቃት ሒደት ያገኘውን ኳስ ወደ ግብ ሞክሮ በግቡ ቋሚ ወደ ውጪ ወጥቶበታል

ቢጫ ካርድ
59′
ተመስገን ካስትሮ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

57′ አዲስ ግደይ ከግራ መስመር እያጠበበ በመግባት በተከላካዮች መሀል ያሾለከለትን ኳስ ባዬ ገዛኸኝ አግኝቶ አልተጠቀመበትም፡፡

55′ ጨዋታው በሚቆራረጥ እንቅስቃሴ ቀጥሏል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሯል፡፡

የእረፍት ሰአት ለውጥ – ሲዳማ ቡና
ኬኔዲ አሽያ ወጥቶ ሐብታሙ ገዛኸኝ ገብቷል፡፡


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በአርባምንጭ መሪነት ተገባዷል፡፡

* የአርባምንጭ አሰልጣኝ በረከት ደሙ ከዳኛ ጋር በፈጠሩት ውዝግብ በቀይ ካርድ ከአሰልጣኞች መቀመጫ እንዲነሱ ተደርጓል፡፡

ጎልልል!!!! አርባምንጭ
39′ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ ምንተስኖት አበራ ሞክሮ አቅጣጫውን ሲስት በጥሩ አቋቋም ላይ የነበረው ላኪ ሳኒ አክርሮ በመምታት በቀድሞ ክለቡ ላይ አስቆጥሯል::

36‘ ባዬ ገዛኸኝ የፍጹም ቅጣት ምቱን መትቶ በግቡ ቀኝ ቋሚ ወደ ውጪ ሰዷታል፡፡

34′ በአዲስ ግደይ ላይ በተሰራ ጥፋት ለሲዳማ የፍጹም ቅጣት ምት ትሰጥቷል፡፡ የአርባምንጭ ተጫዋቾች ውሳኔውን ተቃውመው ከዳኛ ጋር እየተወዛገቡ ይገኛሉ፡፡

30′ ጨዋታው እየተቀዛቀዘ መጥቷል፡፡ በራስ የሜዳ ክልል ከሚደረጉ ቅብብሎች የዘለለ እንቅስቃሴም እየታየ አይገኝም፡፡

ቢጫ ካርድ
18′
ሙጃሂድ መሐመድ የጨዋታውን የመጀመርያ ማስጠንቀቂያ ተመልክቷል፡፡

15′ ጨዋታው ፍጥነት በተሞላበት እንቅስቃሴ ታጅቦ እየተደረገ ይገኛል፡፡

4′ ሲዳማዎች በድጋሚ በግራ መስመር በኩል አደገኛ የግብ እድል ፈጥረው በአንተነህ መሳ ከሽፏል፡፡

2′ ሲዳማዎች በግራ መስመር በኩል ጥሩ የማጥቃት እንቅስቃሴ አድርገው ወደ ውስጥ ቢገቡም አርባምንጮች በቀላሉ ተቆጣጥረውታል፡፡

ተጀመረ!
1′ ጨዋታው በአርባምንጭ ከተማ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

09:30 የሁለቱ ቡድን ተጫዋቾች ወደ ሜዳ ገብተው የክብር እንግዶቹን እየተዋወቁ ይገኛሉ፡፡

ለ3ኛ ደረጃ በተደረገ ጨዋታ ፋሲል ከተማ ከ ወላይታ ድቻ መደበኛውን ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ አጠናቀው በመለያ ምቶች ፋሲል ከተማ 5-4 አሸንፏል፡፡ 


የሲዳማ ቡና አሰላለፍ

1 ፍቅሩ ወዴሳ 

12 ግሩም አሰፋ – 18 ሚኬል አናን – 2 ፈቱዲን ጀማል – 25 ክፍሌ ኪአ 

23 ሙጃሂድ መሐመድ – 6 አምሀ በለጠ

15 አብዱለጢፍ መሐመድ – 3 አሺያ ኬኔዲ – 14 አዲስ ግደይ

9 ባዬ ገዛኸኝ

ተጠባባቂዎች

30 መሳይ አያኖ

17 ዮናታን ፍስሀ

19 አዲስአለም ደበበ

21 ወንድሜነህ አይናለም 

8 ትርታዬ ደመቀ

16 ጸጋዬ ባልቻ

26 ቤን ኮናቴ

10 አብይ በየነ

18 ሚካኤል አሲሳ

7 ምስጋና ወልደዮሀንስ 

27 ሀብታሙ ገዛኸኝ

የአርባምንጭ ከተማ አሰላለፍ

1 አንተነህ መሳ

14 ወርቅይታደል አበበ – 15 ተመስገን ካስትሮ – 5 አንድነት አዳነ – 2 ተካልኝ ደጀኔ 

20 ወንድወሰን ሚልኪያስ – 4 ምንተስኖት አበራ – 25 አለልኝ አዘነ – ወንድሜነህ ዘሪሁን 

16 ዮናታን ከበደ – 11 ላኪ ሰኒ

ተጠባባቂዎች 

79 ሲሳይ ባንጫ 

21 ብሩክ ዋኮ  

16 ታሪኩ ኮራቶ

18 አስጨናቂ ጸጋዬ

19 ገብረሚካኤል ያዕቆብ 

29 ብርሀኑ አዳሙ

8 እስራኤል ሻጉሌ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *