ደደቢት የውጭ ዜጋ አሰልጣኝ ለመቅጠር እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ክለቡ የፖላንድ እና የፔሩ ዜግነት ያላቸው አሰልጣኞችን ሲቪ እየተመለከተ ሲሆን ከሁለቱ አንዱ የክለቡን ፍላጎት የሚያሟሉ ከሆነ ለሰማያዊው ጦር ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ክለቡ ከአሰልጣኝ ቅጥር ጋር በተያያዘ ሃገር ውስጥ ያሉ አሰልጣኞችን ሊቀጥር የሚችለው ከውጭ ሊያመጣቸው ያቀዷቸው አሰልጣኞች ካልተሳኩ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ እ4ስካሁን የ2 የሃገር ውስጥ አሰልጣኞችን ወረቀት እየተመለከቱ እንደሆነም ታውቋል፡፡
ክለቡ ከተጫዋቾች ዝውውር ጋር በተያያዘ እስካሁን ተጫዋቾችን ማስፈረም እንዳልጀመረ ከክለቡ ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ደደቢት ነገ እና ረቡእ የተጫዋቾቹን ኮንትራት የማደስ እንቅስቃሴ እንደሚጀመር የተገለፀ ሲሆን የወጣቱ ተከላካይ አስቻለው ታመነን ኮንትራት ለማራዘም በቃል ደረጃ ከስምምነት መድረሳቸው ታውቋል፡፡ ከራምኬል ሎክ ጋር ስሙ በከፍተኛ ደረጃ የተያያዘው ደደቢት ከተጫዋቹ ጋር እስካሁን ምንም ድርድር እንዳላደረገም አስታውቋል፡፡