ወላይታ ድቻ ናይጄሪያዊ አማካይ አስፈረመ

በርካታ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ እየቀላቀለ የሚገኘው እና ባልተለመደ ሁኔታ ፊቱን የውጪ ሀገር ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾች ላይ ትኩረት ያደረገው የጥሎ ማለፉ ቻምፒዮን ወላይታ ድቻ ናይጄርያዊው አማካይ ሂላሪ ኢኬናን አስፈርሟል፡፡

የ26 አመቱ ኢኬና በተከላካይ አማካይ ስፍራ ላይ የሚጫወት ሲሆን ከ2014 ጀምሮ በሀገሩ ናይጄሪያ ለሰንሻይን ስታር ክለብ፣ ለፖርቹጋሉ ኤዲ ካማቻ እና ለማልታው ቫሌታ ስታር ክለቦች መጫወት ችሏል፡፡ ከ2016 አንስቶ እስከ ተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ድረስ ደግሞ ወደ ስሎቫኪያ አቅንቶ ለሁለተኛ ዲቪዝዮኑ ኤምኤፍኬ ሴካሊካ ተጫውቷል፡፡ በስቴፈን ኬሺ አሰልጣኝነት ዘመንም ለናይጄርያ የቻን ቡድን መጫወት ችሏል፡፡

ለወላይታ ድቻ የአንድ አመት ኮንትራት የፈረመው ኢኬና ከኢማኑኤል ፌቮ (ናይጄርያ)፣ አራፋት ጃኮ (ቶጎ)፣ማሳማ አሴልሞ (ቻድ) በመቀጠል 4ኛው በክለቡ የሚገኝ የውጪ ዜጋ ሆኗል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *