​ከፍተኛ ሊግ ክለቦች ዝግጅት፡ አማራ ውሃ ስራ 

የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (አውስኮድ) አስቀድሞ በኢትዮዽያ ብሔራዊ ሊግ በኋላም በከፍተኛ ሊግ ውድድር ውስጥ ጥሩ ተፎካካሪ በመሆን ቢታወቅም እንዳለው የተጫዋች ጥራት እና ከፍተኛ የገንዘብ አቅም ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደግ ተስኖታል ።

በ2009 ላይ በከፍተኛ ሊጉ በነበረው ተሳትፎ በምድብ ሀ አምስተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው አማራ ውሀ ስራ ለዘንድሮ የውድድር አመት በርካታ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ የሚገኝ ሲሆን ከመስከረም መጀመርያ አንስቶ በዛው በባህርዳር ከተማ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል።

ክለቡ ባሳለፍነው የውድድር አመት በነበረው ጉዞ ውስጥ እንደ ክፍተት የተመለከተው ወደ ክለቡ የሚመጡ ተጨዋቾች በተለያዩ ክለቦች ተዟዙረው በመጫወት የሚታወቁ እና በፍላጎት የማይጫወቱ መሆናቸው መሰረታዊ ክፍተት ሆኖ እንዳገኙት ክለቡ አመራሮች ይናገራሉ። ዘንድሮ በነበረው የዝውውር እንቅስቃሴም ካለፈው ትምህርት በመውሰድ የጨዋታ ፍላጎታቸው የተሻሉ ተጫዋቾች ወደ ክለቡ እንደመጡ ተገልጿል፡፡

የክለቡ አዳዲስ ፈራሚዎች

አውስኮድ ከአምናው ስብስቡ 11 ተጨዋቾችን አስቀርቶ በአዲስ መልክ ቡድኑን ለማጠናከር 15 ተጨዋቾችን ወደ ክለቡ ያመጣ ሲሆን እነሱም በግብ ጠባቂነት ሙሉጌታ አሰፋ (መከላከያ) ከፍያለው ኃይሉ (ኢትዮጵያ መድን) ተጫዋቾች ክብሮም ግርማይ ( ወልዋሎ )፣ ተዘራ መንገሻ ( ባህርዳር ከተማ )፣ እንድሪስ ሰይድ ( መቐለ) ሚኪያስ ደምሴ ( ወራቤ)፣ ሚኪያስ አለማየው ( ወራቤ)፣ ተስሎች ሳይመን ( መድን)፣ ኤርሚያስ ኃይሉ ( አአ ፖሊስ)፣  አብደላ እሸቱ ( ደሴ ከተማ) ፣ ይታያል ዳኛቸው ( ባህርዳር ከተማ )፣ አብዱልከሪም ቃሲም ( ቡራዩ)፣ ሳሙኤል ዮሐንስ ( ንግድ ባንክ)፣ ቴዎድሮስ መንገሻ ( ወላይታ ድቻ/ወልዋሎ )፣ካርሎስ ዳምጠው ( መከላከያ)  ናቸው ።

በአሰልጣኝ አብርሃም መላኩ እና ረዳታቸው እየተመራ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው አውስኮድ በአቋም መፈተሻ ጨዋታ ባህርዳር ከነማን በማሸነፍ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር አቻ በመውጣት የቡድኑን ወቅታዊ አቋም መገምገም ችሏል፡፡ አሰልጣኝ አብርሃም አለሙ በዘንድሮ ቡድናቸው አወቃቀር ደስተኛ እንደሆኑና ከአምናው ውጤት በተሻለ ጥሩ ውጤት ዘንድሮ እንደሚያስመዘግቡ ተናግረው “በአንደኛው ዙር ላይ በምናደርጋቸው ጨዋታዎች ጥንቃቄ አድርገን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለመግባት ጠንክረን እንሰራለን” ብለዋል ።

በከፍተኛ ሊግ በ2010 የውድደር አመት በምድብ ሀ የተመደበው አውስኮድ የመጀመርያውን ጨዋታ የቀድሞ ስያሜውን ኢት ውሃ ስፖርት በመቀየር በአዲስ ስያሜ የሚጠራው ኢኮስኮን ባህርዳር ከተማ ላይ የሚገጥም ይሆናል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *