​አዳማ ከተማ አይቮሪኮስታዊ አማካይ አስፈርሟል

ከሌሎች ክለቦች አንጻር እምብዛም በተጫዋች ዝውውር ላይ ያልተሳተፈው አዳማ ከተማ በክረምቱ ሁለተኛ የውጪ ዜጋ ተጫዋች አስፈርሟል፡፡

የአይቮሪኮስት ዜግነት ያለው የ28 አመቱ ኢስማኤል ሳንጋሪ የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋች ሲሆን ያሳለፈው መልካም የሙከራ ጊዜን ተከትሎ ለክለቡ የአንድ አመት ውል ፈርሟል፡፡ አዳማ በመጨረሻው የአአ ከተማ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ላይም መጫወት ችሏል፡፡

ሳንጋሪ ከአይቮሪኮስቱ ታላቅ ክለብ አሴክ ሚሞሳ አካዳሚ የተገኘ ሲሆን በክለቡም ሁለት አመታትን ተጫውቶ ከማሳለፉ በሞሮኮ ለሳሌ ፣ ቻባብ አትላስ እና ስታዴ ሞሮኮ ፤ በሩማንያው ቪቶሬል ኮንስታንታን እንዲሁም በሱዳኑ አል አህሊ ሸንዲ ተጫውቶ አሳልፏል፡፡ ወደ አዳማ ከመምጣቱ በፊትም ለቱኒዚያው ኦሎምፒክ ቦዚድ ተጫውቷል፡፡

አዳማ ከተማ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የሙከራ እድል ሰጥቶት የነበረው ደቡብ ሱዳናዊው ፒተር ዱስማንን ማስፈሰሙ የሚታወስ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *