​ብሔራዊ ቡድኑ 27 ተጫዋቾች ይዞ ነገ ልምምድ ይጀምራል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ማጣርያ ከሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር እሁድ የመጀመርያ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ከዚህ ቀደም ከጠሯቸው 25 ተጫዋቾች በተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾትን አክለው በነገው እለት ልምምድ እንደሚጀምሩ ታውቋል፡፡

ፌዴሬሽኑ ለጨዋታው የቀረው የዝግጅት ጊዜ አጭር በመሆኑ ለካፍ ያቀረበው የይራዘምልኝ ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ እሁድ 10:00 ላይ በአዲስ አበባ ስታድየም የመጀመርያ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ የመልሱን ጨዋታ ደግሞ ከአንድ ሳምንት በኋላ ኪጋሊ ላይ በማድረግ በድምር ውጤት የሚያሸንፈው ቡድን ወደ ሞሮኮ 2018 የሚያመራ ይሆናል፡፡

የተጠሩ ተጫዋቾች ዝርዝር 

ግብ ጠባቂዎች

ጀማል ጣሰው (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ለአለም ብርሀኑ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ታሪክ ጌትነት (ደደቢት)

ተከላካዮች

አስቻለው ታመነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሳላዲን በርጊቾ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ አበባው ቡታቆ  (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ቴዎድሮስ በቀለ (መከላከያ)፣ ግርማ በቀለ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ደስታ ዮሀንስ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ኄኖክ አዱኛ (ጅማ አባ ጅፋር)

አማካዮች

ምንተስኖት አዳነ  (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሙሉአለም መስፍን (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሱራፌል ዳኛቸው (አዳማ ከተማ)፣ መስኡድ መሐመድ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ሳምሶን ጥላሁን (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ተክሉ ተስፋዬ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ፍሬው ሰለሞን (ሀዋሳ ከተማ)፣ እሸቱ መና (ወላይታ ድቻ)

አጥቂዎች

ጋዲሳ መብራቴ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ አስቻለው ግርማ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ አቡበከር ሳኒ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሳላዲን ሰዒድ (ቅዱስ ጊዮርጊሰ)፣ ዳዋ ሁቴሳ (አዳማ ከተማ)፣ አሜ መሐመድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል (መቀለ ከተማ)፣ ጌታነህ ከበደ (ደደቢት)፣ ምንይሉ ወንድሙ (መከላከያ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *