​ዜና እረፍት | ፌዴራል ዳኛ ሀብቱ ኪሮስ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

ፌዴራል ረዳት ዳኛ ሀብቱ ኪሮስ ዛሬ ረፋድ ላይ በድንገተኛ የልብ ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

ሀብቱ ቅዳሜ እለት በከፍተኛ ሊግ ጅማ ላይ የተካሄደው የጅማ አባ ቡና እና ስልጤ ወራቤ ጨዋታ ላይ ከዳኘ በኋላ ትላንት ወደ አአ ተመልሶ በመኖርያ ቤቱ ተመልሶ ድንገተኛ የልብ ህመም ያጋጠመው ሲሆን ወደ ህክምና ቢያመራም ህይወቱን ማዳን አልተቻለም።

ከ2001 ጀምሮ በፌዴራል ዳኝነት ሲያገለግል የቆየው ሀብቱ ኪሮስ የ2009 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የአመቱ ምስጉን ረዳት ዳኛ ሆኖ ተመርጦ ነበር።

በአዲስ አበባ አዋሬ አካባቢ የተወለደው ሀብቱ ኪሮስ ባለትዳር እና የአንድ ልጅ አባት የነበረ ሲሆን የቀብር ስነስርአቱ  በሀና ማርያም ቤተክርስቲያን በነገው እለት ይፈፀማል።

ሶከር ኢትዮጵያ በፌዴራል ዳኛ ሀብቱ ኪሮስ እረፍት የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀች ለቤተሰቦቹ እና ወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ትመኛለች።

ሀብቱ ኪሮስ ለመጨረሻ ጊዜ የዳኘበት የጅማ አባ ቡና እና ስልጤ ወራቤ ጨዋታ (ከግራ ወደ ቀኝ መጨረሻ ላይ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *