​ዝውውር | ኢትዮጵያ ቡና ተጨማሪ አጥቂ አስፈርሟል

ኢትዮጵያ ቡና በዝውውር መስኮቱ ሁለተኛ የውጪ ተጫዋች ዝውውሩን በማጠናቀቅ ሴኔጋላዊው ባፕቲስቴ ፋዬን በእጁ አስገብቷል።

ለኢትዮጵያ ቡና የዘንድሮው ደካማ የሊግ ጉዞ ውሰጥ ከሚጠቀሱ ዋነኛ ክፍተቶች መካከል የአጥቂ ክፍሉ ይጠቀሳል። ይህንን ስፍራ ለማጠናከር ዩጋንዳዊው ቦባን ዚሪንቱሳን ያስፈረመው ክለቡ ሴኔጋላዊው ባብቲስቴ ፋዬን በአንድ አመት ውል ማስፈረም ችሏል። ቡና የተጫዋቹን ፊርማ ባለፈው ሳምንት (የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት) ማጠናቀቁ የታወቀ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ክለቡነረ ይቀላቀላል ተብሏል። ከሁለተኛው ዙር ጀምሮም የክለቡን መለያ ለብሶ መጫወት እንደሚችል ታውቋል።

የ30 አመቱ ባፕቲስቴ በእግርኳስ ህይወቱ ከ10 በላይ ክለቦች ውስጥ ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን በፖርቱጋል ዝቅተኛ ዲቪዝዮን ( ኦሊቬይራ ፣ ቪዜላ ፣ ቪላ ሚአ ፣ ፔናፊል) ፣ በአንጎላ (ኢንተር ክለብ ፣ ሳግራዳ) በደቡብ አፍሪካ (ፖልክዋኔ) እና በአልባኒያ (ሉፍቴታሪ) ፣ በሮማኒያ (ፒያትራ ኒያአምት) እና በቆጵሮስ (ሴቲንካያ) ተጫውቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *