አርባምንጭ ከተማ እና ላኪ ሰኒ ተለያይተዋል

አርባምንጭ ከተማ በክረምቱ ሲዳማ ቡናን በመልቀቅ ክለቡን ከተቀላቀለው ናይጄርያዊ አጥቂ ላኪ ሳኒ ጋር መለያየቱ ታውቋል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አስከፊ አጀማመርን ያደረገው አርባምንጭ ከተማ በክረምቱ በዝውውር መስኮቱ ባልተለመደ ሁኔታ ሶስት የውጭ ተጫዋቾች ያስፈረመ ቢሆንም የውድድር አመቱ ከመጀመሩ በፊት ከጋናዊው አጥቂ ሰይዱ ባንሴ ጋር መለያየቱ ይታወሳል። አሁን ደግሞ ሌላኛውን ናይጄሪያዊ አጥቂ ላኪ ሳኒን አሰናብቷል። ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፀው ከሆነ ተጫዋቹ በክለቡ እያሳየ ባለው አቋም ደስተኛ ካለመሆናቸው በተጨማሪ አሞኛል በሚል ሰበብ በልምምድ ላይ በተደጋጋሚ ባለመገኘቱ ምክንያት ከተጫዋቹ ጋር ለመለያየት ተገደዋል።

አሁን አሁን ወደ ሀገራችን የሚመጡ የውጭ ተጫዋቾች ከክለቦች ጋር በተለያዩ ምክንያቶች እምብዛም አገልግሎት ሳይሰጡ ወደ ሀገራተው ሲመለሱ ይስተዋላል። በዚህ አመት ብቻ ከውጭ ከመጡ ተጫዋቾች መካከል ፒተር ዱስማን (ደቡብ ሱዳን/አዳማ) ፣ ሂላሪ ኢኬና (ናይጄሪያ/ወላይታ ድቻ) ፣ ሰይዱ ባንሴ (ጋና/አርባምንጭ) ፣ ሮበርት ሴንቴንጎ (ዮጋንዳ/ፋሲል – በድጋሚ ተመልሷል) ፣ ክርስቶፎር አሞስ ኦቢ (ናይጄርያ/ፋሲል) ይጠቀሳሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *