​ጁነይዲ ባሻ የቻን አዘጋጅነት የሚያበስረውን አርማ ለመቀበል ወደ ሞሮኮ ያመራሉ

የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) በ2020 ለማስተናገድ ካፍ እድሉን የሰጣት ኢትዮጵያ በመጪው እሁድ በ2018 እያስተናገደች ካለችው ሞሮኮ እጅ አዘጋጅነቷን የሚያበስር አርማ የምትቀበልበት ስነ-ስርዓት ይኖራል።

በዚህ ስነ-ስርዓት እና የፍፃሜውን ጨዋታ ለመታደም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ፕሬዝደንት ጁኒየዲ ባሻ እና ግዜያዊው ዋና ፀሃፊ ሰለሞን ገብረስላሴ በመጪው ረቡዕ ወደ ስፍራው ያመራሉ። በፍፃሜው ጨዋታ ቀንም የተለመደው የአርማ ርክክብ የካፍ ፕሬዝደንት አህመድ አህመድ በተገኙበት የሚኖር ይሆናል። የርክክቡም ቦታ የፍፃሜ ጨዋታው በሚደረግበት የካዛብላንካው ስታደ መሃመድ አምስተኛ ይሆናል።

ካፍ ኢትዮጵያን አዘጋጅ አድርጎ የመረጠው በዘመነ ኢሳ ሃይቱ ሲሆን በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥም በሚቋቋም ቡድን አማካኝነት ኢትዮጵያን ውድድሩን ለማስተናገድ እያደረገች ያለችውን ዝግጅት የሚቃኝ ይሆናል።

በቻን 2018 ለፍፃሜ ለማለፍ አዘጋጇ ሞሮኮ ከ2014 ቻምፒዮኗ ሊቢያ ጋር ስትፋለም ሱዳን የናይጄሪያን ትገጥማለች።

የአህመድ አስተዳደር የቻን ውድድርን የማስቀረት ፍላጎት እንዳለው በተለያዩ ግዜያት ቢነገርም አሁንም ካፍ ለውድድሩ ትኩረት መስጠቱን ቀጥሎበታል።

ከአቶ ጂኒይዲ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ የምናደርገውን ቆይታ ነገ ምሽት ይጠብቁን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *