ሀሪስተን ሄሱ በቤዢፉት የዓመቱ ምርጥ ቤኒናዊ የስፖርት ሰው ሽልማት እጩዎች ውስጥ ተካተተ

የቤኒን ታዋቂ ጋዜጣ የሆነው ቤዢፉት የዓመቱን የቤኒን ምርጥ የስፖርት ሰው ሽልማት ዕጩዎች አስታወቀ፡፡ እንዳምናው ሁሉ የኢትዮጵያ ቡናው ግብ ጠባቂ ሃሪስተን ሄሱ ለዓመቱ ለዬሱፉ ሴሚዩ የቤኒን ምርጥ ግብ ጠባቂ እጩዎች ዝርዝር ውስጥ ከገቡ ሶስት ግብ ጠባቂዎች አንዱ መሆን ችሏል፡፡ ከሃሪስተን ጋር ተፎካካሪ ሆነው ለአመቱ ምርጥ በረኛ እጩዎች ውስጥ የገቡት ቀድሞ በለሃቭር ሲጫወት የነበረውና አሁን ደግሞ በቱርክ ለማላትያስፖር የሚጫወተው የ33 ዓመቱ ፋብያን ፋርኖል እንዲሁም በፈረንሳይ ለንዮር የሚጫወተው የ24 ዓመቱ ሳቲዩርኒን አላግቤ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ቡናው ሀሪስተን ሄሱ በ2017 ከተደረጉ ጨዋታዎች መካከል በ16 ጨዋታዎች ጎል ሳይቆጠርበት በአንደኝነት የታጨ ሲሆን የአምናው ሻምፒዮን አላግቤ በ11 እና ፋብያን በ7 ጨዋታዎችን ያለግብ በመጨረስ ይከተሉታል፡፡

ከዓመቱ ግብ ጠባቂዎች ባሻገር ባሉ ዘርፎች በእግር ኳስ ልማት ኢሞሩ ቡራይማ በስፖርት ሚኒስቴር የስፖርትና የስፖርት ስልጠና ዳይሬክተር፣ ማግሏር ኦኬ የኢዩ.ኤስ.ኤስ ክለብ ፕሬዚደንት እንዲሁም ዋሃቡ አደም ሻቢ የኮቶኑ ፖርት ክለብ ፕሬዚዳንት እጩ ሆነው ቀርበዋል፡፡

ከዚህ ባሻገር የዓመቱ ምርጥ ቤኒናዊ ተጫዋች፣ በአፍሪካ ውስጥ የሚጫወት ምርጥ ተጫዋች፣ ባለጥምር ዜግነት ምርጥ ቤኒናዊ ተጫዋች የሚሉ ሽልማቶች ያሉት የቤኒን ምርጥ ተጫዋቾች ሽልማት ከዛሬ ጀምሮ ለህዝብ ድምጽ ክፍት የሚሆን ሲሆን ፌብርዋሪ 26 አሸናፊው ይታወቃል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናው ሄሱ ባለፈው ዓመት በአፍሪካ ውስጥ የሚጫወት ምርጥ ቤኒናዊ የሚለውን ሽልማት ያገኘ ሲሆን በቱርኩ ጌንሰልበርጊ እየተጫወተ የሚገኘው የቀድሞው የዌስትብሮም ኮከብ ሰቴፈን ሴሴኞ ማሸነፉ ይታወሳል፡፡ አሁን ሄሱ እጩ የሆነበትን ሽልማት ያገኘው ደግሞ ከዘንድሮ እጩዎች አንዱ የሆነው ሳቱርኒን አላግቤ ነበር፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *