የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅቱን ባለፈው ሳምንት የጀመረ ሲሆን የወዳጅነት ጨዋታዎች እንደሚያካሂድ ተገልጦ ነበር ፡፡
አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ከሞዛምቢክ ብሄራዊ ቡድን ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ ለማድረግ እንዳሰቡ ቢገልጡም ባልታወቀ ምክንያት ተሰርዟል፡፡ አሁን ደግሞ ከአንጎላ እግርኳስ ፈዴሬሽን እስካሁን መልስ አለመስጠቱ ተወርቷል፡፡
የአንጎላ እግርኳስ ፌዴሬሽን በዚህ ሳምንት ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የወዳጅነት ጨዋታውን በሃምሌ መጨረሻ በሉዋንዳ ለማካሄድ ደብዳቤ ቢልክም ፌዴሬሽኑ እስካሁን ምልሽ አልሰጠም፡፡ አንጎላዎች የዋልያዎቹን ሙሉ የደርሶ መልስ የአውሮፕላን ትኬት እና የሆቴል ወጪ ለመሸፈን ቃል ገብተው እንደነበርም ተወርቷል፡፡
ፖርቱጋላዊው ማርያኖ ባሬቶ ከፖርቱጊዝ ተናጋሪ ሃገራት ጋር መልካም ግንኙነት እንዳላቸው በመገመቱ ሌሎች የወዳጅነት ጨዋታዎች ሊያመቻቹ ይችላሉ የሚል ተስፋ አለ፡፡
ብሄራዊ ቡድኑ ከተመረጡት 32 ተጫዋቾች 2/3 ኛ ተጫዋቾችን ይዞ በሃዋሳ ልምምድ በማድግ ላይ ይገኛል፡፡