ተጫዋቾችን የማስጠንቀቅ ተራው የሲዳማ ቡና ሆኗል

የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ለተጫዋቾቻቸው ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ቀጥለዋል። አሁን ደግሞ ተረኛ የሆነው ሲዳማ ቡና ሆኗል። የውጪ ዜጎቹ መሐመድ ኮናቴ ፣ ኬኔዲ አሽያ እና አብዱለጢፍ መሐመድ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤው የደረሳቸው ተጫዋቾች ናቸው።

በክለቡ ከፍተኛ የደሞዝ ክፍያ የሆነው 174 ሺህ ብር የሚከፈለው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ኬኔዲ አሽያ በዝግጅት ወቅት ያሳየውን እንቅስቃሴ በሊጉ በተሰለፈባቸው ጨዋታወች ላይ ማሳየት ባለመቻሉ ከመደበኛ አሰላለፍ ውጭ ተደርጓል። ሌላኛው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቾች የሆነው ኢኳቶሪያል ጊኒያዊው መሀመድ ቤን ኮናቴ እና ጋናዊው የመስመር ተጫዋች መሀመድ አብዱለጢፍ በተደጋጋሚ የገዳት ምክንያቶች በማቅረብ ከልምምድ በመቅረት እንዲሁም የወረደ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴን እያሳዩ በመሆናቸው ክለቡ አቋማቸውን እንዲያሻሽሉ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ለማወቅ ችለናል። በቀጣይ ጨዋታዎች ላይ ይህን ካልተገበሩም ለማሰናበት እንደሚገደድ መግለፁን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *