የቢድቬትስ ዊትሱ አጥቂ ጌታነህ ከበደ ወደ ኢትዮጰያ ሊመለስ ይችላል የሚሉ ጭምጭምታዎች እየተናፈሱ ነው፡፡ ይህን ተከትሎም የአዲስ አበባ ክለቦች ተጫዋቹን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይቷል ተብሏል፡፡ የ2005 የሊጉ ኮከብ ግብ አግቢ በቀድሞ ክለቡ ደደቢት ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚፈለግ ሲሆን በቢድቬትስ ዊትስ ያለውን ኮንትራት ለ1 ተጨማሪ የውድድር ዘመን እንዳራዘመም እየተወራ ነው፡፡
ለተጫዋቹ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደሚገልፁት ተጫዋቹ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለመስማማት ጫፍ እንደደረሰ ቢጠቁሙም ተጫዋቹ ከደቡብ አፍሪካ ለእረፍት ሲመለስ ከክለቡ ጋር ያለውን ውል አራዝሞ መምጣቱ ተወርቷል፡፡ ‹‹ ቅዱስ ጊዮርጊስ መጫወት ብፈልግም በቢድቬትስ ውሌን አራዝሜያለው ›› ማለቱ ተሰምቷል፡፡
ጌታነህ ከበደ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን አመዛኝ ጨዋታዎች በቢድቬትስ ዊትስ ተጠባባቂ ወንበር ላይ አሳልፎ አጠናቋል፡፡
.
ምንጭ – ዛሚ ስፖርት ብሄራዊ (ሬድዮ)