​ወላይታ ድቻ ለተጫዋቾቹ የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማትን አበርክቷል

ወላይታ ድቻ በካፍ የቶታል ካፍ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ትላንት በሀዋሳ አለም አቀፍ ስቴዲየም የዛንዚባሩን ክለብ ዚማሞቶን ገጥሞ 1-0 በማሸነፍ በድምሩ የ2-1 ውጤት ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍን ማረጋገጡን ተከትሎ የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማትን ለቡድኑ አባላት አበርክቷል፡፡

ክለቡ ከትላንቱ ድል በኋላ ለእያንዳንዱ ተጫዋች የ20 ሺህ ብር የማበረታቻ የገንዘብ ድጋፍን ዛሬ አድርጓል፡፡ በቀጣይ ሁለተኛ ማጣሪያውን የግብፁን ኃያል ክለብ ዛማሌክን ከአንድ ወር በኃላ በሜዳው የሚያስተናግድ ሲሆን ያንንም ጫወታ ማሸነፍ የሚችሉ ከሆነ ከዚህም በተሻለ መልኩ ከፍተኛ የማበረታቻ ክፍያን ለማድረግ እንዳሰበም ታውቋል።

ድቻ ባለፈው ሳምንት ዚማሞቶን በመጀመሪያው ማጣሪያ ገጥሞ አንድ አቻ ሲለያይ የ10 ሺህ ብር ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ዛሬ ወደ ሶዶ ሲያመሩ ከፍተኛ አቀባበል እንደሚጠብቀው ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል። ክለቡ የፊታችን ማክሰኞ ወደ ጅማ በማምራት ጅማ አባጅፋርን በሊጉ ተስተካካይ ጨዋታ የሚገጥም ይሆናል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *