ሀዋሳ ዳኜን ለመልቀቅ እያንገራገረ ነው
ከዳሽን ቢራ ጋር ስምምነት ላይ የደረሱት አሰልጣኝ ታረቀኝ አሰፋ ‹‹ዳኜ›› ሀዋሳ ከነማ ባነሳው ቅሬታ ምክንያት የፊርማው ሂደት ተስተጓጉሏል፡፡ ሀዋሳ ከነማባለፈው የውድድር ዘመን አሰልጣኙን ሲቀጥር ያስፈረማቸው ውል ገና ስላልተጠናቀቀ ወደ ሌላ ክለብ የማምራት መብት አይኖራቸውም የሚል አቋም ይዟል፡፡
ዳዊት እስጢፋኖስ በድርድር ላይ ነው
የኢትዮጵያ ቡናው አምበል ዳዊት እስጢፋኖስ ከክለቡ ጋር በኮንትራት ማራዘምያ ዙርያ የሚያደርገው ድርድር እስካሁን መቋጫ አላገኘም ተብሏል፡፡ ክለቡ እና ተጫዋቹ በፊርማ ክፍያው መጠን ላይ ሰፊ ልዩነት ያለቸው ሲሆን ክለቡን መልቀቅ የማይፈልገው ዳዊት ጥሩ ክፍያ እንዲከፈለው ይፈልጋል፡፡
በረከት አዲሱ አዳማ ከነማ ሊቆይ ይችላል
በኢትዮጵያ ቡና እና ደደቢት በጥብቅ የሚፈለገው በረከት አዲሱ ጉዳይ የነገውን የአዳማ ከነማ እና ሱሉልታ ከነማ ወሳኝ የፕሪሚየር ሊግ መግቢያ ጨዋታን ተከትሎ እልባት ያገኛል ተብሏል፡፡ አዳማ ከነማ ጨዋታውን አሸንፎ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱን ካረጋገጠ የኮንትራት ማራዘምያ እና አዳዲስ ተቻዋቾች መግዣ ገንዘብ ይመደብለታል፡፡ በረከት አዲሱ እና ለሎች ወሳኝ ተጫዋቾችም ኮንትራታቸው ለ2 ተጨማሪ አመታት ሊራዘም እንደሚችል ተወርቷል፡፡
የሙከራ እድሎች
የቅዱስ ጊዮርጊሱ ተከላካይ ቢያድግልኝ ኤልያስ በደቡብ አፍሪካ የሚያደርገው ሙከራ በጥሩ ሁኔታ እየተጓዘለት መሆኑ ተወርቷል፡፡ ከቢያድግልኝ በተጨማሪ ሌላው የቅዱስ ጊዮርጊስ ተከላካይ አሉላ ግርማ ከደቡብ አፍሪካ ፣ ግብፅ እና አረብ ሃገራት ጋር ግንኙነት ጀምሯል፡፡
ዳሽን ቢራ በቅዱስ ጊዮርጊስ ተከላካዮች ላይ አነጣጥሯል
ዳሽን ቢራክለቡ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለሙከራ ያመራው ቢያድግልኝ ኤልያስን ለማስፈረም ይፈልጋል፡፡ ተጫዋቹ የሙከራ ጊዜው ካልተሳካ ዳሽን ደደቢትን ቀድሞ ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ሌላው በዳሽን ቢራ የሚፈለገው የቀኝ ተከላካዩ አሉላ ግርማ ነው፡፡ የኮንትራት ማራዘምያ ያልፈረመው አሉላ እንደ ቢያድግልኝ ሁሉ የሙከራ እድሎች ካልተሳኩ ዳሽን ቢራን ሊቀላቀል ይችላል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾቹን ለማቆየት ጥረት ጀምሯል
በርካታ ተጫዋቾች እንደሚለቁበት እየተወራ የሚገኘው ቻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኮንትራታቸው ያለቀባቸው ተጫዋቾችን ማነጋገር መጀመሩ ተሰምቷል፡፡ ክለቡ ከግማሽ ደርዘን በላይ ተጫዋቾቹ ኮንትራት ተገባዷል፡፡
ምንጭ – ዛሚ ስፖርት ብሄራዊ (ሬድዮ)