ሰንዴይ ሙቱኩ ለፋሲል ከተማ ፈረመ

ፋሲል ከተማ ኬንያዊው ሁለገብ ተጫዋች ሰንዴይ ሙቱኩን በአንድ አመት ውል አስፈርሟል።

ሰንደይ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ጥሩ የውድድር አመት ያሳለፈበት ሲዳማ ቡናን ለቆ ድሬዳዋ ከተማን ቢቀላቀልም በምስራቁ ክለብ የተጠበቀውን ያህል እንቅስቃሴ ማድረግ ሳይችል ቀርቶ በትላንትናው እለት ከክለቡ ጋር በስምምነት ውሉን በማፍረስ ወደ ፋሲል ከተማ አምርቷል። እስከ ቀጣዩ አመት አጋማሽ ድረስም የአፄዎቹ ማልያ የሚለብስ ይሆናል።

ፋሲል ከተማ በውድድር አመቱ መጀመርያ ያስፈረማቸው የውጪ ዜጎች ቁጥር 5 የነበረ ቢሆንም ናይጄርያዊው ክርስቶፈር አሞስ ኦቢን በማሰናበቱ አንድ ለውጪ ተጫዋች ቦታ አለው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *