​ታፈሰ ተስፋዬ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ተቀላቀለ

አንጋፋው አጥቂ ታፈሰ ተስፋዬ ከአዳማ ከተማ ጋር በስምምነት በመለያየት በአንድ አመት ኮንትራት ኢትዮ ኤሌክትሪክን ተቀላቅሏል።

በ2007 ክረምት ሀዋሳ ከተማን ለቆ ሁለት አመት ከግማሽ የውድድር ዘመን ያሳለፈበት አዳማ ከተማን የተቀላቀለው ታፈሰ ተስፋዬ በአዳማ የመጀመርያ አመት ቆይታው በ15 ጎሎች የፕሪምየር ሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ቢያጠናቅቅም አምና እና ዘንድሮ በጉዳት ፣ እድሜ እና በቦታው ባለው ከፍተኛ ፉክክር ምክንያት እምብዛም የመሰለፍ እድል ማግኘት አለመቻሉን ተከትሎ ከቀናት በፊት ከክለቡ ጋር በስምምነት በመለያየት ወደ አሳዳጊ ክለቡ ከረጅም አመት በኋላ የሚመልሰውን ዝውውር ፈፅሟል። በዛሬው እለት ከቡድኑ ጋር ልምምድ መስራቱም ታውቋል።

5 ጊዜ የፕሪምየር ሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ በማጠናቀቅ ብቸኛ የሆነው ታፈሰ ተስፋዬ በ1994 ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ዋናው ቡድን ያደገ ሲሆን በ1997 ወደ ኢትዮጵያ ቡና አምርቶ እስከ 2002 ቆይቷል። ከየመን የአንድ አመት ቆይታ በኋላም በቡና ፣ ሀዋሳ ከተማ እና አዳማ ከተማ አሳልፏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *