ወልዋሎ ከአራት ተጫዋቾች ጋር ተለያይቷል

በዘንድሮው የውድድር ዘመት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን የተቀላቀለው ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ካስፈረማቸው ተጫዋቾች መካከል 4 ተጫዋቾቹን በአቋም መውረድ እና ጉዳት ምክንያት አሰናብቷል፡፡

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለቡን ተቀላቅሎ የቡድኑ ሶስተኛ ተመራጭ ግብ ጠባቂ የነበረው በለጠ ተስፋዬ እና አዳማ ከተማን በመልቀቅ ወደ ክለቡ አምርቶ በመጀመርያ አሰላለፍ ውስጥ መካተት ያልቻለው ቢንያም አየለ የሚጠበቅባቸውን አቋም አላሳዩም በሚል ሲቀነሱ በጉዳት ምክንያት በውድድር ዘመኑ ጥቂት ጨዋታዎችን ብቻ ያደረጉት ብሩክ አየለ እና እዮብ ወልደ ማርያም ደግሞ በስምምነት ከክለቡ ጋር የተለያዩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

በተያያዘ ዜና በውድድር ዓመቱ አጋማሽ የዝውውር መስኮት አለምነህ ግርማ ፣ ማናዬ ፋንቱ እና ሪችሞንድ አዶንጎን ያስፈረመው ወልዋሎ ሌላው ቡድኑን ለመቀላቀል ተስማምቶ የነበረው ታዲዮስ ወልዴ ባቀረበው የተጋነነ ክፍያ ምክንያት እንዳልተቀላቀለ ከክለቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *