የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ድልድል ይፋ ሆኗል

ለሶስተኛ ጊዜ ከሚያዝያ 6 እስከ 20 በቡሩንዲ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያም በምድብ ለ ተደልድላለች፡፡

ድልድሉ ይህንን ይመስላል፡-

ምድብ ሀ

ዩጋንዳ፣ ታንዛንያ፣ ዛንዚባር፣ ሱዳን

ምድብ ለ

ኢትዮጵያ፣ ቡሩንዲ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ

ኢትዮጵያ የመጀመርያ የምድብ ጨዋታዋን ከሶማሊያ ጋር በማድረግ የምትጀመር ይሆናል፡፡ በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ የመጨረሻ 23 ተጫዋቾችን በመያዝ ለውድድሩ ዝግጅቱን እያከናወነ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *