ቻን 2020 | የካፍ ገምጋሚዎች አዲስ አበባ ገብተዋል

በ2020 የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) የምታስተናግደው ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ውድድሩን ለማስተናገድ ያላትን ዝግጁነት የሚገመግም የካፍ ልዑክ አዲስ አበባ መግባቱ ታውቋል።

የካፍ ገምጋሚ ልዑካን በዋነኝነት ስታዲየሞች እና መሰረተ ልማቶችን የሚመለከቱ ሲሆን ለዚህ ውድድር በፌዴሬሽኑ አማካኝነት እንደተመዘገቡ የተነገረላቸው የባህርዳር፣ ሀዋሳ፣ መቐለ፣ አደይ አበባ እና ድሬዳዋ ስቴዲየሞችን ተዟዙረው ይገመግማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ስታድየሞቹ በአሁነለ ወቅት ሙሉ በሙሉ ያልተጠናቀቁ ሲሆን የድሬዳዋ ስታድየምም በማስፋፍያ ስራ ላይ ይገኛል። ሆኖም በቀሩት 20 ወራት ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።