ዘላለም ሽፈራው የወልዲያ አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የወልዲያ ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸውን ክለቡ በይፋዊ የፌስቡክ ገፅ አስታውቋል።

ወልዲያ የውድድር ዓመቱን በዘማርያም ወልደጊዮርጊስ አሰልጣኝነት ቢጀምርም ወልዲያ ከ ፋሲል ከተማ ባደረጉት ጨዋታ በተከሰተው ስርዓት አልበኝነት የአንድ ዓመት ቅጣት በመቀጣታቸው ቡድኑ በምክትሉ ኃይማኖት ግርማ እየተመራ በውድድሩ መቀጠሉ ይታወሳል።

ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በውድድር ዓመቱ አጋማሽ የተለያዩት አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ያለፉትን ወራት ያለ ስራ ቆይተው በመጨረሻም ርዝመቱ ባልተጠቀሰ ውል ወልዲያን ተቀላቅለዋል። በነገው እለትም በይፋ ስራቸውን እንደሚጀምሩ ክለቡ አስታውቋል።

አሰልጣኝ ዘላለም ከዚህ ቀደም በደቡብ ፖሊስ፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና፣ ደደቢት፣ አዳማ ከተማ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሰርተዋል።