ከፍተኛ ሊግ ሀ | ወሎ ኮምቦልቻ ሲያሸንፍ የካ ከሜዳው ውጪ ነጥብ ተጋርቷል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ 18ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ተጀምሯል። ወሎ ኮምቦልቻ ሲያሸንፍ የካ ክፍለ ከተማ ከሜዳው ውጪ ነጥብ ተጋርቷል።
አክሱም ላይ የካ ክፍለከተማን ያስተናደገው አክሱም ከተማ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል። አክሱሞች በ68ኛው ደቂቃ ሰላማዊ ጎል አማካኝነት ቀዳሚ ቢሆኑም የካዎች በ86ኛው ደቂቃ ላይ አቻ የሚያደርጋቸውን ጎል አስቆጥረዋል። ሁለተኛው ዙር ከተጀመረ ወዲህ ውጤቱን እያሻሻለ የሚገኘው የካ ባለፉት 3 ጨዋታዎች ሽንፈት ባለማስተናገድ ያለመውረድ ተስፋውን ማለምለም ችሏል።
ኮምቦልቻ ላይ ወሎ ኮምበልቻ ሱሉልታ ከተማን አስተናግዶ 2-0 በማሸነፍ ቢያንስ ደሴ ከተማ ማክሰኞ ጨዋታ እስኪያደርግ ድረስ የደረጃውን ግርጌ መላቀቅ ችሏል። የወሎ ኮምቦልቻን በ10ኛው (ፍፁም ቅጣት ምት) እና 85ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው አሸናፊ መሳይ ነው። ድሉ ለአዲሱ አሰልጣኝ ብርሀኔ ገብረእግዚአብሔር የመጀመርያ ሆኖም ተመዝግበል።

የከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሀ ማክሰኞ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይቀጥላል፡-

የደረጃ ሰንጠረዥ

ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች