ኢትዮጵያዊቷ አጥቂ ለታንዛኒያው ክለብ ለመፈረም ከጫፍ ደርሳለች።

በኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እየተጫወተች የምትገኘው መሳይ ተመስገን ወደ ታንዛኒያው ያንግ አፍሪካንስ ማምራቷን ከቀናት በፊት አሳውቀናችሁ ነበር።
መሻዋን ከወጣቶች ስፖርት አካዳሚ አድርጋ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ መቻል እና ንግድ ባንክ ቆይታ የነበራት አጥቂዋ በኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሁሉም የዕድሜ እርከኖች መጫወት የቻለችው መሳይ አሁን በያንግ አፍሪካንስ የሕክምና ምርመራ ላይ እንደምትገኝ እና ምናልባትም ከሰዓታት በኋላ በይፋ እንደምትፈርም ሶከር ኢትዮጵያ የተጫዋቿ ወኪል ከሆነው ታዛ ስፖርትስ ማኔጅመንት ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል።
በታንዛኒያ ያንግ አፍሪካንስ አረጋሽ ካልሳ ፣ በሲምባ ኩዊንስ ሴናፍ ዋቁማ እየተጫወቱ እንደሚገኙ ይታወቃል።

