የሱዳኑ ወሳኝ ተጫዋች መሐመድ ዒሳ ከጨዋታው በፊት ምን አለ?

የሱዳኑ ወሳኝ ተጫዋች መሐመድ ዒሳ ከጨዋታው በፊት ምን አለ?

“በተቻለ መጠን ብዙ ግቦችን ለማስቆጠር እንሞክራለን”

“የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጥፎ ቡድን አይደለም”

ቀደም ብለን የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ እና የብሔራዊ ቡድናችን አምበል ያሬድ ባየህ እንዲሁም የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ከጨዋታው በፊት የሰጡትን ሀሳብ ወደ እናንተ ማቅረባችን ይታወሳል። አሁን ደግሞ የሱዳኑ የፊት መስመር ተጫዋች መሐመድ ዒሳ ከጨዋታው በፊት በስፍራው ለሚገኙ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሐን የሰጠውን ሃሳብ ወደ እናንተ እናደርሳለን።

ወደ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ እንኳን በደህና መጣህ ፤ ከኢትዮጵያ ጋር ስለሚደረገው ጨዋታ ያለህን ሀሳብ ብታጋራን ?

በጥሩ የራስ መተማመን እንገኛለን። በመጀመሪያው ጨዋታ ላይ ሦስት ነጥብ ማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነው። ሁሉም እዚህ ያለው ተጫዋች ዝግጁ ነው። እንዲሁም ጨዋታውን በጉጉት እየጠበቅን ነው።

ከዚህ ቀደም እዚህ ሜዳ ግብ አስቆጥረህ ነበር ፤
አሁንስ ?

አዎ የመጀመሪያው ዕቅዳችን ነው፤ በተቻለ ፍጥነት ግብ ለማስቆጠር አቅደናል፤ በቡድናችን ውስጥም ጥሩ ጥሩ አጥቂዎች አሉ። በተቻለ መጠን ብዙ ግቦችን ለማስቆጠር እንሞክራለን።

ስለ ተጋጣሚያቹህ ምን ትላለህ ?

ከባድ ይሆናል፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጥፎ ቡድን አይደለም፤ በቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ ለማሳተፍ ይፈልጋሉ። ነገር ግን እኛም ጠንካራ ቡድን ነው ያለን የምንችለውን ሁሉ ለማድረግም እንሞክራለን።