የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 25ኛ ሳምንት ተራዝሟል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 25ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የሚካሄዱበት ቀናት ላይ ሽግሽግ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ምርጫ በመጪው እሁድ ግንቦት 26 በአፋር ሰመራ የሚካሄድ ሲሆን የፕሪምየር ሊጉ 25ኛ ሳምንት ጨዋታዎችም በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ እንዲካሄዱ መርሐ ግብር ወጥቶላቸው ነበር። ሆኖም ከፌዴሬሽኑ ባገኘነው መረጃ መሠረት ውድድሩ ከምርጫው ጋር በማይጋጭ መልኩ እንዲቀጥል በማሰብ የጨዋታዎቹ ቀናት ወደ ማክሰኞ ተገፍተዋል።

ከመርሐ ግብሩ የቀን ለውጥ ውጪ እያንዳንዱ ጨዋታ መቼ እንደሚደረግ ፌዴሬሽኑ ያላሳወቀ ሲሆን ከሰዓታት በኀኋላ የተሻሻለውን መርሐ ግብር ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።