ለ2015 የሞሮኮ አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ምድብ ውስጥ ለመግባት በተደረገ የቅድመ ማጣርያ ጨዋታ ማላዊ ቤኒንን አሸንፋ የነ ኢትዮጵያን ምድብ መቀላቀሏን አረጋግጣለች፡፡
በኮቶኑ በተካሄደው የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታ 1-0 ተሸንፋ የተመለሰችው ማላዊ በሜዳዋ ባደረገችው የመልስ ጨዋታ ሙሉውን 90 ደቂቃ 1-0 በሆነ ውጤት ያጠናቀቁ ሲሆን አሸናፊዎቹን ለመለየት በተሰጠው የመለያ ምት ማላዊ 4-3 አሸንፋ ወደ ምድብ ማጣርያው መቀላቀሏን አረጋግጣለች፡፡
የምድብ ማጣርያ ውድድሮች በነሀሴ ወር መጨረሻ ሲጀምሩ ኢትዮጵያ ከአልጄርያ ፣ ማሊ ከ ማላዊ የመጀመርያ ጨዋቸውን ያደርጋሉ፡፡