ብሄራዊ ቡድኑ በአበበ ቢቂላ ልምምዱን አድርጓል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለ2017 የጋቦን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የሚያደርገውን ዝግጅት ቀጥሏል፡፡ ባለፈው አርብ በአቋም መለኪያ ጨዋታ በሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድን 3-1 ተሸንፎ ወደ አዲስ አበባ የተመለሰው ብሄራዊ ቡድኑ ለሲሸልሱ ጨዋታ ዝግጅት የሚያደርገውን ልምምድ ቀጥሏል፡፡ ትላንት በአዲስ አበባ ስታድየም ልምምዱን ያከናወነ ሲሆን ዛሬ ረፋድ 4፡00 ላይ ደግሞ በአበበ ቢቂላ ስታድየም ልምምዱን አድርጓል፡፡ በመጪው ቅዳሜ የሲሸልስ እና የኢትዮጵያ ጨዋታን የሚያስተናግደው ስታዲየም ስታደ ሊኒት የአርቴፊሻል ሳር ሜዳ በመሆኑ ብሄራዊ ቡደኑ ዝግጅቱን እያደረገ ያለው በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ነው፡፡ አበበ ቢቂላ ስታዲየምም የአርቴፊሻል ሳር ሜዳ ነው፡፡

የዋሊዎቹ ግብ ጠባቂዎች

በልምምድ ፕሮግራሙ የኤምሲ አልጀርሱ አጥቂ ሳላዲን ሰኢድ የዋልያዎቹን ስብስብ የተቀላቀለ ሲሆን አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ቡድኑን ለሁለት ከፍለው በግማሽ ሜዳ በማጫወት ልምምድ አሰርተዋል፡፡ ትላንት በተደረገው ልምምድ ሽመልስ በቀለ ፣ ዋሊድ አታ እና ጌታነህ ከበደ ቡድኑን ተቀላቅለው ልምምድ ሰርተዋል፡፡
ዋልያዎቹ ወደ ሲሸልስ ነገ እንደሚበሩ የሚጠበቅ ሲሆን በመጪው ቅዳሜ ከሲሸልስ ብሄራዊ ቡድን ጋር 2ኛ የምድብ ማጣርያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ 8 ተጫዎቾችን ከስብስባቸው ውጪ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ በመጀመርያው የምድብ ጨዋታ ሌሶቶን 2-1 በማሸነፍ የጋቦን ጉዞውን በድል መጀመሩ ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *