ኢትዮጵያ ቡና ዳንኤል ደምሱን አስፈርሟል

በዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ ቡና በቀጣይ አመት ተጠናክሮ ለመቅረብ እና ዘንድሮ የነበሩበትን ክፍተቶች ለማስተካከል ነባር ተጨዋቾችን እየቀነሰ አዳዲስ ተጨዋቾችንም ወደ ቡድኑ እየቀላቀለ ይገኛል።

በአሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜዝ የሚሰለጥኑት ቡናማዎቹ በዛሬው እለት ዳንኤል ደምሱን ማስፈረማቸው የታወቀ ሲሆን ዳንኤልም ወደ ቡድኑ የተቀላቀለ ተጫዋች ሆኗል። በ2008 ክረምት ባህር ዳር ከተማን ለቆ ወደ ወልዲያ ያመራው ዳንኤል በክለቡ ሁለት የውድድር ዓመታትን አሳልፏል። ዳንኤል ከሚታወቅበት የመሃል ሜዳ ተጨዋችነት በተጨማሪ የተከላካይ መስመር ተጨዋች ሆኖ ሲጫወት በውድድር ዘመኑ የታየ ሲሆን የሁለገብነት ብቃቱ ለአሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜዝ አማራጭ ተብሎ ይታሰባል።

ኢትዮጵያ ቡና ከዘጠኝ ተጫዋቾቾች ጋር እንደማይቀጥል የታወቀ ሲሆን በአዳዲስ ተጫዋቾች ለመተካት በዝውውር ገበያው ላይ በንቃት ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል።