የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የዋንጫ እና የመለያ ጨዋታዎች – ቀጥታ ስርጭት

(በሽረ እንዳስላሴ እና ጅማ አባ ቡና ጨዋታ ላይ አተኩረን ዋና ዋና ጉዳዮችን በEdit እናደርሳችኋላን።)
_________

ተጠናቀቀ | ባህር ዳር ከተማ 0-1 ደቡብ ፖሊስ
(36′ ኤሪክ ሙራንዳ)

ተጠናቀቀ |  ሽረ እንዳሥላሴ 2-1 ጅማ አባ ቡና

(72′ ሸዊት ዮሀንስ 76′ ሰዒድ ሁሴን | 4′ ብዙዓየሁ እንደሻው )

__________

90′ የሽረው ግብ ጠባቂ ሀፍቶም ቢሰጠኝ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግዷል።

76′ ተቀይሮ የገባው ሰዒድ ሁሴን በሁለት ደቂቃ የሜዳ ቆይታው ከግብ ጠባቂ የተተፋን ኳስ አስቆጥሮ ሽረ ወደ መሪነት ተሸጋግሯል።

73′ ሸዊት ዮሀንስ ከግራ መስመር አክርሮ በመመታት ድንቅ ጎል አስቆጥሮ ሽረን አቻ አደረገ።


69′ ሽረዎች በድጋሚ እጅግ ለግብ የቀረበ ኳስ አምክነዋል። ሸዊት ከግብ ጠባቂው ፊት ያገኘውን ኳስ በአናት ሰዶታል።

61′ ሽረዎች መልካም የግብ ማግባት አጋጣሚ አግኝተው ሸዊት ዮሀንስ የግቡ ቋሚ መልሶበታል። 

60′ በሁለተኛው አጋማሽ ሽረዎች የተሻለ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ።

10:18 ሁለተኛው አጋማሽ ተጀመረ።

10:05 – የመጀመርያው አጋማሽ በአባ ቡና 1-0 መሪነት ተጠናቀቀ።

– 

30′ በፈጣን እንቅርቃሴ የተጀመረው ጨዋታ ቀስ በቀስ ተቀዛቅዟል። አባ ቡና ወደ ግብ በመድረስ የተሻለ ነው።

4′ ብዙአየሁ እንደሻው ከርቀት የተሻገረለትን ኳስ በግሩም አጨራረስ አስቆጥሮ አባ ቡናን ቀዳሚ አድርጓል።

09:14 ሽረዎች የተገቢነት ክስ አስመዝግበው ጨዋታው ተጀምሯል።

09:10 የህዝብ መዝሙር ተዘምሯል።

09:05 ቡድኖች ወደ ሜዳ ገብተው ከእንግዶች ጋር እየተዋወቁ ይገኛሉ።

08:55 ሁለቱም ሜዳዎች የሚደረጉ ጨዋታዎች ሊጀምሩ ጥቂት ደቂቃ ቀርቷቸዋል። ቡድኖቹ አሟሙቀው ወደ ሜዳ ገብተዋል።