አዲስ አበባ ከተማ መኮንን ገብረዮሀንስን አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሚወዳደረው አዲስ አበባ ከተማ የሊጉ ልምድ ያላቸው መኮንን ገብረዮሀንስን አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል። 

አዲስ አበባ ከተማ ከአሰልጣኙ ጋር ከሳምንት በፊት በቃል ደረጃ ከስምምነት ደርሶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ፊርማቸውን ለማኖር ከአውስኮድ መልቀቂያቸውን እስኪወስዱ ሲጠበቅ ነበር። አሰልጣኙ በሳምንቱ መጨረሻ መልቀቂያቸውን በመውሰዳቸው ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር በሁለት ዓመት ውል ለመስራት መስማማታቸው ታውቋል።

አሰልጣኝ መኮንን ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ውሀ ስፖርትን (አሁን ኢኮስኮ) በ2004፣ ዳሽን ቢራን በ2005 እንዲሁም ጅማ አባ ጅፋርን በ2009 እየመሩ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያሳደጉ ሲሆን ባህር ዳር ከተማ እና አውስኮድ ሌሎች ካሰለጠኑባቸው ክለቦች መካከል ናቸው።