ኢትዮጵያ ከ ኬንያ – እውነታዎች

በ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኬንያን 10:00 ላይ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም ያስተናግዳል። ጨዋታውን አስመልክቶ በሁለቱ ሀገራት የእርስ በእርስ ግንኙነት ተመስርተን ያሰናዳናቸውን ጥቂት እውነታዎች እነሆ፡-

መገጣጠም

– ኢትዮጵያ እና ኬንያ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከ48 ዓመታት በኋላ ይገናኛሉ። በ1972 (እ.አ.አ) ካሜሩን አስተናግዳው ለነበረው ውድድር ለማለፍ የመጀመርያ ዙር ማጣርያ ጨዋታዎች በ1962 ተከናውነው ኬንያ በድምር ውጤት 3-0 አሸንፋ አልፋለች። (አአ ላይ 1-0፤ ኬንያ ላይ 2-0 በማሸነፍ) 

– ከ48 ዓመታት በኋላ ዘንድሮ ሲገናኙም ጨዋታውን ሲያደርጉ በድጋሚ በካሜሩን አስተናጋጅነት ከሚከናወን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጋር ተገጣጥሟል። 

ጎሎች

– በህዳር 4 ቀን 1956 አዲስ አበባ ላይ በተደረገ የቶኪዮ ኦሎምፒክ ማጣርያ ኢትዮጵያ ኬንያት 7-1 ያሸነፈችበት ጨዋታ በሁለቱ ቡድኖች የእርስ በእርስ ግንኙነት ታሪክ ከፍተኛው ነው። በወቅቱ ኢትዮጵያ በድምር ውጤት አሸንፋ ወደ ተከታይ ዙር ብታልፍም በሞሮኮ ተሸንፋ ወድቃለች። 

– መጋቢት 26 ቀን 1953 ኬንያ ኢትዮጵያን አዲስ አበባ ላይ 5-4 ያሸነፈችበት የወዳጅነት ጨዋታ በሁለቱ ሀገራት የእርስ በእርስ ግንኙነት ታሪክ በአንድ ጨተታ በርካታ ግብ (9) የተቆጠረበት ነው።
የመጀመርያ ግንኙነት

– ሁለቱ ሀገራት ለመጀመርያ ጊዜ የተገናኙት በመጋቢት 30 ቀን 1953 አዲስ አበባ ላይ በተደረገ የወዳጅነት ጨዋታ ነበር። በወቅቱ ኢትዮጵያ 6-1 አሸንፋለች። 

የእርስ በእርስ ግንኙነት በቁጥሮች

ተጫወቱ –  32

ኢትዮጵያ አሸነፈች – 12

አቻ – 8 

ኬንያ አሸነፈች – 12

ኢትዮጵያ አስቆጠረች – 48

ኬንያ አስቆጠረች – 42

በዚህ ወር..

– ሁለቱ ሀገራት ዛሬ ጨዋታቸውን በሚያደርጉበት ወር (ኦክቶበር) ከዚህ ቀደም ሶስት ጊዜ ተገናኝተው ኬንያ ሁለቱን (በ1961 እና 1963) ስታሸንፍ በ1984 ያደረጉት ጨዋታ አቻ ተጠናቋል። (ዓመቶቹ በአውሮፓውያን አቆጣጠር ነው።)

ሁለቱ ሀገራት ኢትዮጵያ ላይ ያደረጓቸው ጨዋታዎች 

ተጫወቱ – 15

ኢትዮጵያ አሸነፈች – 8 (34 ጎሎች)

አቻ – 4 

ኬንያ – 3 (21 ጎሎች)

– ኬንያ ለመጨረሻ ጊዜ ዋልያዎቹን ኢትዮጵያ ላይ የገጠመችው ሰኔ 2007 ሲሆን የዛሬው ጨዋታ በሚደረግበት ባህር ዳር ስታድየም ለቻን ማጣርያ ተጫውተው ኢትዮጵያ 2-0 አሸንፋለች። 

– ኬንያ ለመጨረሻ ጊዜ በኢትዮጵያ ሜዳ ዋልያዎቹን ያሸነፈችው ነሀሴ 10 ቀን 2002 አበበ ቢቂላ ላይ በተደረገ የወዳጅነት ጨዋታ ነበር። በወቀኑ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ናይጄርያ/ብሪታንያዊው ኤፊ ኦኑራ ነበሩ።

የመጨረሻ አምስት የእርስ በእርስ ግንኙነቶች

ሰኔ 27 ቀን 2007 ኬንያ 0-0 ኢትዮጵያ (ቻን ማጣርያ)

ሰኔ 14 ቀን 2007 ኢትዮጵያ 2-0 ኬንያ (ቻን ማጣርያ)

ህዳር 18 ቀን 2005 ኢትዮጵያ 0-0 ኬንያ (ሴካፋ)

ህዳር 21 ቀን 2004 ኬንያ 3-1 ኢትዮጵያ (ሴካፋ)

ህዳር 21 ቀን 2003 ኢትዮጵያ 0-2 ኬንያ (ሴካፋ)