ለሙከራ ወደ ፖርቱጋል አቅንተው የነበሩት ሳላዲን በርጊቾ እና ናትናኤል ዘለቀ የሙከራ ጊዜያቸው ባለመሳካቱ ወደ ሃገር ቤት ትላንት ሌሊት ገብተዋል፡፡ በፖርቱጋሉ ሲዲ ፌሬንሴ ክለብ የሙከራ ጊዜ በማሳለፍ ላይ የነበሩት ሁለቱ ተጫዋቾች በፈረንሳይ ሌላ የሙከራ ጊዜ እንደሚያሳልፉ ቢነገርም ሙከራዎች ሳይሳኩ ወደ ሃገር ቤት ተመልሰዋል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዳስታወቀው ሁለቱ ተጫዋቾች በመጪው ማክሰኞ ውላቸውን ያድሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ናትናኤል ወደ ፖርቱጋል ከማቅናቱ በፊት ከክለቡጋር የለውን ውል ለ2 አመት ለማራዘም በቃል ደረጃ የተስማማ ሲሆን ውሉን የጠናቀቀው ተከላካዩ ሳላዲን በርጊቾ ደግሞ የፖርቱጋል ሙከራው ካልተሳካ ውል እንደሚፈርም በተስማማመው መሰረት ፊርማውን ያኖራል፡፡
በሙከራ እድሉ ምክንያት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተቀንሰው የነበሩት ሁለቱ ተጫዋቾች ወደ ዋልያዎቹ ስብስብ ይመለሳሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡ ከሁለቱ ጋር አብሮ ተቀንሶ የነበረው ራምኬል ሎክ በድጋሚ ለብሄራዊ ቡድን መጠራቱ ይታወሳል፡፡