ኢትዮጵያ ከ ጋና – ቀጥታ ስርጭት

እሁድ ኅዳር 9 ቀን 2011
FT ኢትዮጵያ🇪🇹 0-2 🇬🇭ጋና

3′ ጆርዳን አየው
22′ ጆርዳን አየው (ፍ)

ጨዋታው በጋና 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

90′ አራተኛው ዳኛ ተጨማሪ 4 ደቂቃ አሳይቷል።

90′ ኡመድ ኡኩሪ ከቀኝ መስመር አጥብቦ በመግባት ወደ ጎል የላከው ኳስ ለጥቂት የግቡን ቋሚ ታካ ወጥታለች።

88′ የተጫዋች ቅያሪ – ጋና
ጆርዳን አዬው
ጆናታን ሜንሳህ

80′ ምንይሉ ወንድሙ የግል ጥረቱን ተጠቅሞ ሶስት የጋና ተጫዋቾችን አልፎ ከጋና የግብ ክልል ጠርዝ ላይ አክርሮ የሞከረው ኳስ የጋናው ግብጠባቂ ይዞበታል

78′ የተጫዋች ቅያሪ – ኢትዮጵያ
 ቢኒያም በላይ
 አማኑኤል ገብረሚካኤል

 76′ አህመድ ረሺድ

73′ የተጫዋች ቅያሪ – ጋና
 ክሪስቲያን አትሱ
 ናና አፖማህ

72′ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሁለተኛ አጋማሽ ከጋና በተሻለ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል

71′ የተጫዋች ቅያሪ – ኢትዮጵያ
 አዲስ ግደይ
 ሳምሶን ጥላሁን

66′ አዲስ ግደይ ከማዕዘን ያሻማውን ኳስ ምንይሉ በግንባሩ በመግጨት ቢሞክርም የጋናው ግብጠባቂ ሪቻርድ ኦፎረሐ አድኖበታል፡፡

65′ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በጥሩ ቅብብል ወደ ጋና የግብ ክልል ከደረሱ በኃላ ምንይሉ ወንድሙ ባደረገው ደካማ የሆነ የውሳኔ አሰጣጣጥ ኳሱ ሊባክን ችሏል

60′ ዑመድ ኡኩሪ ከቀኝ መስመር ያሻሻማው ኳስ በጋና ተጫዋቾች ተገጭቶ ሲመልስ ጋቶች ፓኖም በቀጥታ ወደ ግብ የላካት ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል

58′ የተጫዋች ቅያሪ – ጋና

ቶማስ ፓርቴይ

አፍሪይ አክዋህ

57′ የተጫዋች ቅያሪ – ኢትዮጵያ

ደስታ ዮሀንስ

አህመድ ረሺድ

55′ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሁለተኛው አጋማሽ በመጠኑም ቢሆን የተነቃቃ ይመስላል ነገርግን አሁንም ግን በጋና የሜዳ ክልል በመጠኑ ጠጋ ብለው በርከት ያሉ የጎንዮሽ ቅብብሎችን ብቻ ነው ማድረግ እየቻሉ ያሉት::

46′ አዲስ ግደይ በጋና የግብ ክልል ጠርዝ ላይ አግኝቶ የሞከረው ኳስ የጋናው ግብ ጠባቂ በቀላሉ ይዞበታል::

11:02 ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሯል::


እረፍት!

 45+1′ አስቻለው ታመነ

45′ የእለቱ አራተኛ ዳኛ 2 ተጨማሪ ደቂቃዎችን አሳይቷል

41′ አበበ ጥላሁን ከጋና ተከላካዮች ጀርባ በግሩም ሁኔታ ለአብዱልከሪም መሀመድ ያሳለፈለትን ኳስ አብዱልከሪም በግሩም ሁኔታ ከተቆጣጠረ በኃላ ከአዲስ ግደይ ለማቀበል የሞከረውና የጋና ተጫዋቾች ያቋረጡበት ኳስ በኢትዮጵያ በኩል የመጀመሪያው አጋማሽ እጅግ አስቆጪ አጋጣሚ ነበር

37′ ጨዋታ ቀዝቀዝ ብሎ እየተካሄደ ይገኛል::

30′ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ኳስ በሚይዙበት ወቅት በተቃራኒ ሜዳ ላይ በቁጥር በርከት ብለው ቢገኙም የጋናን የመከላከል አደረጃጀት ግን ለመስበር እየተቸገሩ ይገኛል::

25′ ኢትዮጵያዎች በመልሶ ማጥቃት ያገኙትን ኳስ ኡመድ ኡኩሪ ለምንይሉ ወንድሞ በግሩም ሁኔታ ቢያሳልፍለትም ምንይሉ ወደ ግብ የላከው ኳስ ግን ኢላማውን ሳይጠብቅ ቀርቷል::


ጎል ጋና!!!

23′  ሙባረክ ዋካሶ ላይ የኢትዮጵያ ተጫዋቾች በሰሩት ጥፋት የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ጆርዳን አየው በጨዋታው ሁለተኛ ግቡን አስቆጥሯል


 22′ አበበ ጥላሁን

22′ ፍፁም ቅጣት ምት

20′ አስቻለው ታመነ በጋና ተጫዋቾች ጫና የተሳሳተውን አደገኛ ኳስ አማኑኤል ቦአትንግ ወደ ግብ የላከው ኳስ የኢትዮጵያ ተከላካዮች ተደርበው ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል::

19′ ኡመድ ኡኩሪ ያሳለፈለትን ኳስ ተጠቅሞ ከሳጥን ውጪ በቀጥታ አክርሮ የመታውን ኳስ የጋናው ግብጠባቂ ይዞበታል፡፡

*አስቻለው ታመነ የህክምና እርዳታ ተደርጎለት ወደ ሜዳ ተመልሷል::

15′ በጨዋታው የመጀመሪያ ደቂቃ ላይ ከተቆጠረችው ግብ በዘለለ በጨዋታው የመጀመሪያ ደቂቃዎች ተመጣጣኝ የሚባል እንቅስቃሴ እየተመለከትን እንገኛለን::

13′ አስቻለው ታመነ ባጋጠመው ጉዳት ሜዳ ላይ ወድቆ የህክምና ክትትል እየተደረገለት ይገኛል::

10′ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች በራሳቸው ሜዳ ላይ በጋና ተጫዋቾች እየደረሰባቸው ካለው ጫና የተነሳ ለመቀባበል የሚሞክሯቸው ኳሶች ስኬታማ አይደሉም::

6′ በመጀመሪያ ደቂቃ ግብ እንደመቆጠሩ በስታዲየሙ ያለው ድባብ መቀዛቀዝ ይታይበታል


ጎል ጋና!!! ጆርዳን አየው
3′ የጋናው የመስመር ተከላካይ ሀሪሰን አፉል በረጅሙ ያሻማውን ኳስ የኢትዮጵያ ተከላካዮች መዘናጋትን ተከትሎ ጆርዳን አየው በቀላሉ ያገኘውን ኳስ በቀላሉ አስቆጥሯል::


10:01 ጨዋታው ተጀምሯል


09:58 የሁለተ ሀገራት የህዝብ መዝሙር እየተዘመረ ይገኛል::🇪🇹 🇬🇭


[AdSense-B]


አሰላለፍ
ኢትዮጵያ ጋና
22 አቤል ማሞ
2 አ/ከሪም መሐመድ
15 አስቻለው ታመነ
5 አበበ ጥላሁን
12 ደስታ ዮሀንስ
6 ጋቶች ፓኖም
18 ሸመልስ በቀለ (አ)
10 ቢንያም በላይ
11 ኡመድ ኡኩሪ
14 አዲስ ግደይ
17 ምንይሉ ወንድሙ
1 ሪቻርድ ኦፎሪ
2 ሐሪሰን አፉል
17 ለሞር አግቤንዬኑ
12 ኑሁ ካሲም
15 ጆን ቦዬ
11 ሙባረክ ዋካሶ
10 አንድሬ አዬው (አ)
7 ክሪስቲያን አትሱ
5 ቶማስ ፓርቴይ
9 ጆርዳን አዬው
14 ኢሚኑኤል ቦአቴንግ
ተጠባባቂዎች ተጠባባቂዎች
1 ሳምሶን አሰፋ
3 አህመድ ረሺድ
4 አንተነህ ተስፋዬ
7 አቤል ያለው
8 ሳምሶን ጥላሁን
13 ተመስገን ካስትሮ
16 ዳንኤል ደምሴ
19 ከነዓን ማርክነህ
20 ሙሉዓለም መስፍን
21 አማኑኤል ገ/ሚካኤል
16 ላውረንስ አቲ
13 አንዲ ይአዶም
4 ጆናታን ሜንሳህ
18 ናና አፖማህ
6 አፍሪዬ አኳህ
3 አሳሞአህ ጂያን
8 ማጂድ ዋሪስ
ዳኞች
 ዋና – ቪክቶር ጎሜዝ (ደቡብ አፍሪካ)
1ኛ ረዳት – ዛኬሌ ቱሲ (ደቡብ አፍሪካ)
2ኛ ረዳት – ሴሎ ሞሺዲ (ደቡብ አፍሪካ)
ውድድር  | የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ
ቦታ |  አዲስ አበባ ስታድየም
ሰዓት | 10:00

ጤና ይስጥልን

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ምስተኛ የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ ጋናን ታስተናግዳለች፡፡ ከ10፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታድየም የሚደረገውን ይህን ጨዋታም በቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት በሶከር ኢትዮጵያ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

መልካም ቆይታ