አንዋር ያሲን ከኢትዮጵያ ቡና ሊለቅ ይችላል

የኢትዮጵያ ቡና ምክትል አሰልጣኝ አንዋር ያሲን ለክለቡ የልቀቁኝ ደብዳቤ ማስገባቱ ተነግሯል፡፡ አንዋር አምና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እግርኳስ ቡድንን ለቆ ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለ ሲሆን፤ የአሰልጣኝ ጥላሁን መንገሻ ምክትል ሆኖ ክለቡን አገልግሏል፡፡ ከአሰልጣኝ ጥላሁን ስንብት በኃላም በዋና አሰልጣኝነት ቡድኑን በፕሪምየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ መርቷል፡፡ አንዋር ከዋና አሰልጣኙ ሰርቢያዊው ድራጋን ፖፓዲች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ክለቡን ለመልቀቅ እንደወሰነ ተዘግቧል፡፡
በጉዳዩ ላይ ለሶከር ኢትዮጵያ አስተያየታቸው የሰጡት የኢትዮጵያ ቡና ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሙልጌታ ደሳለኝ
“አንዋር የልቀቁኝ ደብዳቤ ዓርብ ዕለት አስገብቷል፡፡ ብሄራዊ ትያትር በተደረገው ዝግጅት ላይ እና በሲቲ ካፑ የመክፈቻ ጨዋታ ላይ አልተገኘም፡፡ እስከዓርብ ድረስ ከክለቡ ጋር ቆይቷል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ጉዳዩን እያጤነ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *