የአአ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለዳኞች የሰጠው ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ

የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለሁለት ቀናት የሰጠው የዳኞችን ሙያ ማሻሸያ ስልጠና ዛሬ ተጠነቀቀ።

በካፍ ኢንስትራክተር ሽፈራው እሸቴ አሰልጣኝነት ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ስፖርት እና ትምህርት ስልጠና ማዕከል በተሰጠው ስልጠና በከተማው የሚገኙ ከ20 በላይ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ዳኞች ተካፍለዋል። ትላንት በተጀመረው ስልጠና ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ኃይለየሱስ ፍስሀ (ኢንጅነር) በከተማችን እግር ኳስን በዘመናዊነት ለመምራት ቁልፍ የሆኑ ዳኞች ከአዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች ጋር ራሳቸውን እያበቁ ሙያውን በብቃት እንዲመሩ ታስቦ መሰጠቱን ተናግረዋል። በተለይ በዘርፉ የካበተ ዕውቀትና ልምድ ያላቸው ኢንስትራክተር ሽፈራው እሸቴ ለ2 ቀናት መስጠታቸው ልዩ ዕድል መሆኑን ነው ፕሬዝዳንቱ የገለፁት። ትኩረቱን በተሻሻሉ አዳዲስ የዳኝነት ህጎች ላይ መሰረት ባደረው በዚህ ስልጠና ሰልጣኞች ጠቃሚ ነገሮች እንዳገኙበት ተናግረው ፌዴሬሽኑ ይህንን ስልጠና በቀጣይ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

በሌላ ዜና የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የውስጥ ውድድሮች የሆኑት የከፍተኛ ዲቪዝዮን፣ አንደኛ ዲቪዝዮን እና የሴቶች ውድድር የጀመረ ሲሆን የኤምአርአይ ምርመራው በተለያዩ ምክንያቶች በፍጥነት አለመጠናቀቁን ተከትሎ ከ17 ዓመት በታች የወንዶች ውድድር እስካሁን ያልጀመረ መሆኑ ታውቋል። በቅርቡ ውድድሩን ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ መሆኑ እና ውድድሩ የሚካሄድባቸውን ሜዳዎች በበቂ ሁኔታ እድሳት እየተደርጎላቸው ለጨዋታው ዝግጁ እንደተደረጉም ተነግሮናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *