ድሬዳዋ ከተማ ይግባኝ ጠየቀ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በኢታሙና ኤይሙኔ ላይ በጣለው የ8 ጨዋታ እገዳ ላይ ክለቡ ድሬዳዋ ከተማ ይግባኝ ጠይቋል።

በ6ኛው ሳምንት ሶዶ ላይ 1-1 በተጠናቀቀው የወላይታ ድቻ እና ድሬዳዋ ከተማ ጨዋታ ፍፃሜ ላይ ናሚቢያዊው አጥቂ ኢታሙና ኬይሙኔ የድቻው ተከላካይ ሙባረክ ሽኩርን በቡጢ ተማቷል በሚል የዲሲፕሊን ኮሚቴው በዚህ ሳምንት የ8 ጨዋታ እገዳ ያስተላለፈበት ሲሆን ድሬዳዋ ከተማም ቅጣቱ የተጋነነ መሆኑን በመጥቀስ ተጫዋቹ የዘረኝነት ስድቦችና ድርጊቶች ሲፈፀምበት የነበረ ከመሆኑ፣ ለሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ እንግዳ እንደመሆኑ እንዲሁም ከዚህ በፊት የዲሲፕሊን ሪከርድ ያልነበረበት ከመሆኑ አንፃር ውሳኔው በድጋሚ እንዲታይለት ጠይቋል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *