የአሰልጣኞች አስተያየት | ወላይታ ድቻ 1-1 ወልዋሎ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ጨዋታ ወላይታ ድቻና እና ወልዋሎ 1-1 ከተለያዩ በኃላ የሁለቱ ክለብ አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል፡፡

” ዕድል ከኛ ጋር ስላልሆነች ነጥብ ተጋርተናል” ዘነበ ፍሰሀ – ወላይታ ድቻ 

ስለጨዋታው

ስንገባ ጀምሮ የነበረው መንፈስ ጥሩ አልነበረም። ተጫዋቾቼ እየተሰደቡ ነበር ወደ ሜዳ የገቡት የ። ክለቡን የሚወዱ ግን ሲያበረታቱ ነበር የቆዩት። ሜዳ ላይ ሁላችንም እየተጠራን እንሰደብ ነበር። በተቻለ መጠን ውጤት አስመዝግበን ለመውጣት ሞክረናል። ተጫዋቾቼ ጥሩ የሚባል ተጋድሎን አድርገዋል። የሚያስደስት ጨዋታን ነበር ማድረግ የቻልነው። ፍፁም ታግለዋል፤ ዕድል ከኛ ጋር ስላልሆነች ግን ነጥብ ተጋርተናል፡፡

ስለ ተቃውሞው

ያን ያህል ቡድኑ ያለበት ደረጃ የሚያስከፋ አይደለም። ያለንበት ደረጃ ተጫዋቾቼ እየተሰደቡ ሊጫወቱ አይችሉም። በእልህ ደግሞ የሚያደርጉትን ነገር እያጡም ስለሆነ የዛሬው ጨዋታ እንደ ጨዋታ መልካም ነው። በጣም ተጋድለዋል፤ ጥሩ ነገር ሰርተዋል፡፡ እድለኛ ሳንሆን ያጣነው ውጤት ነው። ይህ ደግሞ እግር ኳስ ነው። እኔም ደግሞ እየተሰደብኩ በቡድኑ ውስጥ መቀጠል ይከብደኛል፡፡

” ተጫዋቾቼ ላደረጉት ተጋድሎ ምስጋና አለኝ” ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም – ወልዋሎ 

ስለጨዋታው

አብዛኛዎቹ ተጫዋቾቼ አንድ አንድ ብቻ ልምምድ ነው የሰሩት። ወደ ስምንት የሚጠጉም ተጫዋቾች ጉዳት ላይ ነበሩ። በዚህ ሁኔታ ሆነን ነው የገባው። ተጋጣሚያችን ወላይታ ድቻ እንደ ቡድን ጥሩ ነበሩ። ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ነበር። የሚከተሉት አጨዋወት ረጃጅም ነበር፤ ወደ ሳጥን በሚላክ ተፅዕኖ ለመፍጠር ያለመ ነበር። እኛ ደግሞ ጥንቃቄ እየመረጥን ለመጫወት በመልሶ ማጥቃት በሚገኙ ዕድሎች ለመጠቀም ነበር ያሰብነው። በአጠቃላይ ተመጣጣኝ ጨዋታ ነበር። እኛ በሰራነው ስህተት ቢቆጠርብንም ተስፋ ሳንቆርጥ ከሜዳችን ውጭ በመጫወታችን ውጤት ይዘናል። በርካታ ጉዳት እያለብን ተጫዋቾቼ ላደረጉት ተጋድሎ ምስጋና አለኝ። የወላይታ ድቻ ደጋፊዎችም ላሳዩን ደስ የሚል አቀባበል በአክብሮት ላመሰግናቸው እወዳለሁ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *