ሀላባ ከተማ ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ስድስተኛ ሳምንት ታኅሳስ 28 ሀላባ ላይ ሀላባ ከተማ ከኢትዮጵያ መድን ያደረጉት ጨዋታ በ76ኛው ደቂቃ የዕለቱ ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ ከተመልካች በተወረወረ ድንጋይ መፈንከቱን ተከትሎ መቋረጡ የሚታወስ ነው፡፡ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የዲሲፕሊን ኮሚቴም በሀላባ ከተማ ላይ የቅጣት ውሳኔ ወስኗል፡፡

ዋና ዋናዎቹ ውሳኔዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. 150 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት

2. ግብ ሳይቆጠርበት ዘልቆ የነበረውና የተቋረጠው ጨዋታ ለመድን 3-0 ሸናፊነት በፎርፌ እንዲሰጥ፡፡

3. በቀጣይ የሚያደርጋቸውን ሁለት የሜዳው ጨዋታዎች ከሀላባ 200 ኪ/ሜ ርቀት በሚገኙ ሜዳዎች እንዲያከናውን

4. የዕለቱ ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ በደረሰበት ጉዳት ለህክምና የወጣውን ወጪ እንዲተካ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *