ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታን ይመራሉ

የ2018/19 የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ሦስተኛ የምድብ ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ሲከናወኑ የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታን ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ይመሩታል።

በምድብ ለ ከሁለት ጨዋታዎች አራት ነጥቦች በመሰብሰብ ከላይ የተቀመጡት የደቡብ አፍሪካው ኦርላንዶ ፓይሬትስ እና የቱኒዚያው ኤስፔራንስ ደ ቱኒስ የምድቡ መሪ ለመሆን ቅዳሜ ምሽት ይጫወታሉ። ጆሀንስበርግ ኦርላንዶ ስታድየም ላይ የሚካሄደውን ጨዋታም በዋና ዳኝነት በዓምላክ ተሰማ የሚዳኝ ሲሆን ረዘም ያለ ጊዜን ከባምላክ ጋር አብረው የመምራት ልምድ ያላቸው ክንዴ ሙሴ እና ትግል ግዛው በረዳትነት ይዳኛሉ። ለሚ ንጉሴም በአራተኛ ዳኝነት አብሯቸው ይጓዛል።

ከወር በፊት በተደረገው የ2018 ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ኤስፔራንስ ከ አል አህሊ ያደረጉትን ጨዋታ የመራው በዓምላክ በዓለም ክለቦች ዋንጫ ላይ አንድ ጨዋታ የዳኘ ሲሆን በዘንድሮው የቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ውድድር የመጀመርያ ጨዋታውን የሚዳኝ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *