አጫጭር የብሄራዊ ቡድን ዜናዎች

ብሄራዊ ቡድናችን ረፋዱ ላይ ልምምድ ሰርቷል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የዛሬ ልምምዱን ረፋድ ላይ አድርጓል፡፡ ዋሊድ አታም ከቡድኑ ጋር የመጀመርያ ልምምዱን ሰርቷል፡፡

በዛሬው ፕሮግራም ለብሄራዊ ቡድን ከተጠሩት 26 ተጫዋቾች (23 ከሃገር ውስጥ እና 3 ከሃገር ውጪ ክለቦች) መካከል ልምምድ ያልሰራው አሁንም በማረፍያ ቤት ዪገኘው ራምኬ ሎክ ብቻ ነው፡፡

አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ በዛሬው የልምምድ ፕሮግራም ጠንካራ ኳሶችን ወደ ግብ የመምታት ቴክኒኮች እና የጭንቅላት ኳስ ልምድ ሲያሰሩ የተስተዋለ ሲሆን ግብ ጠባቂዎቹም በጠንካራ ምቶች ሲፈተሹ አርፍደዋል፡፡

ዘግይቶ ቡድኑን የተቀላቀለው የጊንኪልቢሪጊው ተከላካይ ዋሊድ አታ ከቡድኑ ተነጥሎ ልምምድ ሲያደርግ ከአየሩ ሁኔታ ጋር ለመላመድ ተቸግሮ ታይቷል፡፡

IMG_8511
ዛሬ ልምምድ የጀመረው ዋሊድ

 

የኮንጎ ብሄራዊ ቡድን ማምሻውን አዲስ አበባ ይገባል

የሪፑብሊክ ኦፍ ኮንጎ ብሄራዊ ቡድን ቅዳሜ ላለበት ጨዋታ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ እንደሚገባ ታውቋል፡፡ የልኡካን ቡድኑ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይመጣል ተብሎ ሲጠበቅ በራሳቸው ቻርተርድ አውሮፕላን እንደሚመጡና ደብረዳሞ ሆቴል እንደሚያርፉ ተነግሯል፡፡

 

ራምኬል ሎክ ለኮንጎው ጨዋታ የመድረሱ ጉዳይ የበቃለት ይመስላል

የብሄራዊ ቡድኑ አጥቂ ራምኬ ሎክ በዚህ ሳምንት መጀመርያ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለበት እለት ጀምሮ አሁንም በማረፍያ ቤት ይገኛል፡፡ በአሁኑ ሰአትም ኮተቤ አካባቢ በሚገኘው የየካ ክፍለከተማ ፖሊስ ጣቢያ በህግ ቁጥጥር ስር ይገኛል፡፡

የራምኬል የክስ ፋይል በፍርድ ቤት የሚታየው በነገው እለት ረፋድ ላይ ሲሆን ከእስር ቢለቀቅ እንኳን ከማክሰኞ ጀምሮ ልምምድ ያልሰራ በመሆኑ ለቅዳሜው ጨዋታ ብቁ ይሆናል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ራምኬል ለመልሱ ጨዋታ ወደ ኮንጎ ከሚጓዘው የብሄራዊ ቡድን ልኡክ ላይካተት እንደሚችልም ከፌዴሬሽኑ አካባቢ ያገኘናቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

© Soccer Ethiopia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *