የከፍተኛ ሊግ አጫጭር መረጃዎች

የምድብ ለ ተስተካካይ ጨዋታ

በ10ኛው ሳምንት ያልተደረገው የሀምበሪቾ ዱራሜ እና ሀላባ ከተማ ተስተካካይ መርሀ ግብር ዛሬ ተከናውኖ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል። እንግዳው ቡድን በ19ኛው ደቂቃ በአቡሽ ደርቤ ቀዳሚ ግብ አስቆጥሮ በሀላባ መሪነት 1-0 ወደ መልበሻ ክፍል ሲያመሩ ከዕረፍት መልስ ለባለሜዳዎቹ በ65ኛው ደቂቃ አላዛር አድማሱ ያአቻነቱን ግብ አስቆጥሯል።


የግማሽ ዓመት ስብሰባ

የእግርኳስ ፌዴሬሽኑ የከፍተኛ ሊግ አወዳዳሪ የመጀመሪያውን ዙር ሊያጠናቅቅ ጥቂት ጨዋታዋች እየቀሩት የሁለተኛውን ዙር መርሀ ግብር ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን የመጀመሪያው ዙር ግምገማ መጋቢት 17 ሊያደርግ እንዳሰበ ተገልጿል።

ይግባኝ

ሀላባ ላይ በ6ኛው ሳምንት በተከሰተው ድርጊት መቶ ሀምሳ ሺ ብር እና ሁለት የሜዳውን ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ እንዲጫወት በዲስፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ የተላለፈበት ሀላባ ከተማ ይግባኝ ብሎ የቅጣት ማቅለያ ተደርጎላታል። ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሀላባ ያቀረበውን ማመልከቻ ከመረመረ በኋላ የገንዘብ ቅጣቱን ወደ 30 ሺህ ብር ዝቅ ሲያደርግ አንድ የሜዳ ቅጣቱም ወደ አንድ ዝቅ አድርጓል። የመድን ሶስት ነጥብ እና ሶስት ንፁህ ጎሎች ግን በድጋሚ ፀድቀዋል።

አሰልጣኝ ቅጥር

አሰልጣኝ አረጋይ ወንድሙ ወደ ደሴ አምርተዋል። በዝንድሮ ዓመት ወልዲያን ሲያሰለጥኑ የነበረው አረጋዊ በግማሽ ዓመት ቆይታው የተለያይተው በ8ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ደሴ ከተማን ለማስልጠን ፊርማቸውን አስቀምጠዋል።

ቀጣይ ጨዋታዎች

በምድብ ሐ ተስተካካይ ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ። ማክሰኞ የካቲት 26 ቡታጅራ ከተማ ከ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ እንዲሁም ነቀምት ከተማ ከ ካፋ ቡና በተመሳሳይ 9:00 ይጫወታሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *