ወልዋሎ ከሁለት ተጫዋቾች ጋር ተለያየ

በሊጉ የዘንድሮው የውድድር አመት ከፋይናንስ ጋር በተያያዙ ችግሮች እየታገለ በመጀመሪያው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ወጣ ገባ አቋምን እያሳየ ማጠናቀቅ የቻለው እና በቅርቡ ከአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም ጋር በስምምነት የተለያየው እና በቅርቡ ደግሞ ዮሀንስ ሳህሌን ለቀጣዮቹ ስድስት ወራት የሾመው ወልዋሎ አሁን ደግሞ ከሁለት ተጫዋቾች ጋርም ዛሬ በይፋ በስምምነት ሊለያይ ችሏል።

ባለፈው የውድድር ዓመት ድሬዳዋ ከተማን በመልቀቅ ወደ ወልዋሎ ያመራው የመሀል ተከላካዩ ተስፋዬ ዲባባ ከክለቡ የተለያየ ቀዳሚው ተጫዋች ነው። የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና፣ ሙገር እና ባንክ ተጫዋች በክለቡ ካለፈው ዓመት አንፃር እምብዛም በክለቡ የመሰለፍ ዕድልን ማግኘት ሳይችል ቀርቷል፡፡ 


ሌላኛው ከክለቡ የተለያየው ግብ ጠባቂው ዮሀንስ ሽኩር ነው። ፋሲል ከነማን ከለቀቀ በኋላ ወደ ወልዋሎ በማምራት በክለቡ በአብዛኛው ጨዋታ ላይ በመሰለፍ ሲጫወት የነበረው እና ዘንድሮው በአብላዚዝ ኬይታ የተሰላፊነት እድሉን ተነጥቋል። ሁለቱም ተጫዋቾች በክለቡ ቀሪ የስድስት ወራት ኮንትራትም ነበራቸው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *