ወልዋሎ ከአንድ ተጫዋቾች ጋር ሲለያይ አንድ ተጫዋች ወደ ዋናው ቡድን አሳድጓል

በትላንትናው ዕለት ከሁለት ተጫዋቾች ጋር በስምምነት የተለያዩት ቢጫ ለባሾቹ ከሮቤል አስራት ጋር በስምምነት ሲለያዩ ሽሻይ መዝገቦን ወደ ዋናው ቡድን አሳድገዋል።

አዲስ አስልጣኝ በመቅጠር ቀድመው ወደ ሁለተኛ ዙር ዝግጅት የገቡት ወልዋሎዎች በዓመቱ መጀመርያ ካስፈረሙት የግራ መስመር ተከላካይ ሮቤል አስራት በስምምነት ተለያይተዋል።

በ2009 ጅማ አባጅፋር የከፍተኛ ሊጉ ዋንጫ አንስቶ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድግ የቡድኑ አባል የነበረው ይህ ተጫዋች በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያ ቡናን ቢቀላቀልም ብዙም ሳይቆይ ከቡድኑ ጋር ተለያይቶ ነበር በዚህ ዓመት መጀመርያ ቢጫ ለባሾቹን የተቀላቀለው።


ወደ ዋናው ቡድን ያደገው ተስፈኛው ግብ ጠባቂ ሽሻይ መዝገቦ ነው። ላለፉት ሁለት ዓመታት በትግራይ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ውጤታማ የነበረው ወልዋሎ ቢ አባል የነበረው ይህ ግብ ጠባቂ በቅርቡ ከቡድኑን በስምምነት የለቀቀው ዮሃንስ ሽኩርን ቦታ ይተካል።

በ2010 ወደ ፕሪምየር ሊጉ ካደጉ በኋላ ተጫዋች ሳያሳድጉ የቆዩት ወልዋሎዎች በዓመቱ መጀመርያ በረከት ገብረእግዚአብሄር እና ሰመረ ካሕሳይ ወደ ዋናው ቡድን ማሳደጋቸው ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *