አሰልጣኝ ተመስገን ዳና እና ሀዋሳ ከተማ ሊለያዩ ነው

ከወጣት ቡድን ጀምሮ በዋና አሰልጣኝነት ያገለገለው እና ያለፉትን ስድስት ወራት በሀዋሳ ዋናው ቡድን ምክትል አሰልጣኝ በመሆን ሲሰራ የቆየው አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ከቡድኑ ጋር ለመለያየት የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብቷል።

ባለፉት ዓመታት በወጣቶች እግርኳስ ላይ ስኬታማ ከሆኑ አሰልጣኞች መካወል ግንባር ቀደም የሆነው አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ዘንድሮ ነበር የሀዋሳ የዋናው ቡድን ምክትል አሰልጣኝ እንዲያገለግል የተመረጠው። ሀዋሳ ከተማ በአንደኛው ዙር ላደረገው ጥሩ ጉዞ ከአሰልጣኝ አዲሴ ካሴ ጋር በመሆን ስኬታማ ጊዜ ማሳለፍ ችሏል።

አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ዛሬ ለክለቡ የመልቀቂያ ደብዳቤ ያስገባ ሲሆን ከክለቡ ጋር ለመለያየት እንደምክንያት ያቀረበው ክለቡ ሲቀጥረው ቃል ገብቶለት የነበረውን ያለፉት ወራት ሊፈፅምለት ባለመቻሉ እንደሆነ ተናግሯል።

በቀጣይ ክለቡ የተመስገንን ጥያቄ ተቀብሎ በምክትል አሰልጣኝነት እንዲቀጥል ያደርገዋል ወይስ መልቀቅያውን በመቀበል ይለያያሉ የሚለው በቀጣይ የሚጠበቅ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *