ድሬዳዋ ከተማ ከአራት ተጫዋቾቹ ጋር ተለያይቷል


ድሬዳዋ ከተማ ከወራት በፊት ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው ስድስት ተጫዋቾች መካከል ከአራቱ ጋር መለያየቱን አስታውቋል፡፡

በ2010 ሲዳማ ቡናን በመልቀቅ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ያመራው የግራ መስመር ተከላካዩ ወሰኑ ማዜ ከክለቡ ከተለያዩ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና፣ ወልዲያ እና ንግድ ባንክ ተጫዋች በዘንድሮው የውድድር ዓመት በድሬዳዋ የተሰላፊነት እድልን ካለፈው አመት አንፃር ማግኘትም አልቻለም፡፡

ሌላኛው ከክለቡ የተለያየው ዮናታን ከበደ ነው። ከዚህ ቀደም በሀዋሳ፣ ኤሌክትሪክ፣ አዳማ፣ አርባምንጭ እና ወላይታ ድቻ የተጫወተው ዮናታን በአንድ ዓመት ውል ዘንድሮ ድሬዳዋን ቢቀላቀልም ቀሪ የስድስት ወራት ውል እየቀረው ተለያይቷል፡፡

ኤሌክትሪክን በመልቀቅ ወደ ድሬዳዋ አምርቶ የነበረውና በክለቡ የቋሚነት ቦታን ለማግኘት ተቸግሮ የቆየው ኃይሌ እሸቱ እና ጊኒያዊው የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ሲላ አብዱላሂ ከተቀናሽ ተጫዋቾች መካከል ተካተዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *