ድሬዳዋ ከተማ የውሰት ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

ለጅማ አባጅፋር እግርኳሰ ክለብ ኤርሚያስ ኃይሉን በውሰት እንዲሰጡት በደብዳቤ የጠየቀው ድሬዳዋ ከተማ ጥያቄው ተቀባይነት አገኘ።

በሁለተኛው ዙር የውድድር ዘመን ራሱን ከወራጅ ቀጠና ለማራቅ በዝውውሩ ላይ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው ድሬደዋ ከተማ በቅርቡ የጅማ አባ ጅፋሩ የመስመር አጥቂ ኤርሚያስ ኃይሉን በውሰት እንዲሰጡት ለጅማ አባጅፋር በደብዳቤ መጠየቁ ይታወሳል። የቀረበውን ጥያቄ የተመለከተው የጅማ አባጅፋር እግርኳስ ክለብ አመራሮች ኤርሚያስ ኃይሉን በውሰት ለመስጠት ከስምምነት ደርሰዋል።

ድሬደዋ ከተማ ኤርሚያስን በውሰት ማግኘቱን ተከትሎ በአጥቂ በኩል ያለበትን ችግር በተወሰነ መልኩ ይቀርፍለታል ተብሎ ይገመታል።

ኤርምያስ በኒያላ ፣በዳሽን ቢራ ፣ በፋሲል ከነማ እና ጅማ አባ ጅፋር የተጫወተባቸው ክለቦች ናቸው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *